ሰበር ዜና) መንግስት የአሕባሽ ስልጠናን ዳግም ለማስጀመር የ313 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ከመጅሊስ ጋር ተፈራረመ

የመጅሊሱ ፕሬዚዳንትና ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮች ስምምነቱ ላይ እንዳይገኙ ተደርጓል
(ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው) የፌደራል ጉዳያዮች ሚኒስቴርና የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት (መጅሊስ) የአህባሽን ስልጠና ዳግም ለማስቀጠል ከስምምነት ደረሱ፡፡ ስምምነቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሚያዚያ 3/2005 እለተ ቅዳሜ በፌዴራል መጅሊስ ቢሮ ነው፡፡ እንደምንጫችን ገላፃ ስምምነቱ የተካሄደዉ በዶ/ር ሽፈራዉና በመጅሊሱ ዋና ፀሀፊ አቶ ሙሀመድ አሊ፣ የአዲስ አበባ ተወካይ እንዲሁም የቀድሞ የትግራይ መጅሊስ ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የፌዴራል መጅሊስ ም/ፕረዚዳንት በሆኑት አቶ ከድር መሀከል ነው፡፡ ምንጩ አያይዞም በመሰረቱ መንግስት ከሾማቸዉ ስራ አስፈፃሚዎች ዉስጥ ዋናዉን ፕሬዚዳንት ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ስራ አስፈጻሚዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ መጂሊስ ከመንግስት በቀጥታ የሚመጣላቸዉን ትዕዛዝ ተቀብለን አንተገብርም በማለት ላይ ሲገኙ የመጅሊሱ ዋና ፀሀፊና ም/ፕሬዚዳንቱ ግን ትእዛዞችን በቀጥታ በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡በቃሊቲ የመሪዎቻችን እና የሌሎች ወንድሞች መጠየቂያ ቆይታ እንዲያጥር ተደረገ
የባለፈው ቅዳሜ ስምምነትም ያለ ምንም እክል እንዲፈጸም የተደረገዉ ከመንግስት በቀጥታ የሚሰጥ ትእዛዝ አንፈፅምም በማለት ሲሞግቱ ከነበሩት አመራሮች መካከል ዋና ዋናዎችን ሆን ተብሎ በስራ ምክንያት ከአካባቢው በማራቅ ነው ተብሏል፡፡ በዚህም መሰረት የመጅሊሱ ዋና ፕሬዚዳንትንና የድሬዳዋዉን ተወካይ የሀጅና ኡምራ ስራ ስምምነት እንዲያደርጉ ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመላክ፣ የአፋሩን ተወካይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የክልል መጂሊሶች የስራ አፈፃፀም ግምገማ እዲወጡ በማመቻቸትና ሌሎችንም ስብሰባዉ ላይ እዳይካፈሉ በማድረግ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የመንግስት ዋና ታማኝ የሆኑት ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ከድር ማህሙድ አና ዋና ፀሀፌዉ አቶ ሙሀመድ አሊ ጋር የአህባሽ ስልጠና እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የህገ-መንግስት ስልጠና በሚል ስም (ሽፋን) በተጠናከረ መልኩ ዳግም ተጀምሮ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ እንዲሰጥ የ313 ሚሊየን ብር ፕሮፖዛል ሰርተዉ አቅርበዉ በዶ/ር ሺፈራዉ ፀድቆላቸዉ ወደስራ እንደገሚቡ ተስማምተዋል፡፡ እንደምጫችን ገለፃ በአሁኑ ወቅት በመጅሊስ የሂሳብ አካዉንት ውስጥ ያለዉ ብር በጣም አናሳ ሲሆን እንተለመደዉ ወጪዉን መንግስት ሊሸፍነዉ እንደሆነ ተገምቷል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ መንግስት አሁንም መንግስት ‹‹አክራሪነትን በማስወገድ›› ስም በሃይማኖታችን ውስጥ እጁን አስረዝሞ ማስገባቱንና ከዚህ ቀደም ሲፈጽማቸው ከነበሩ ድርጊቶች ሊታቀብ አለመፍቀዱ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋና ፕሬዚዳንቱ በአሁኑ ወቅት ካሉበት ሳኡዲ አረቢያ ሆነዉ ይህ ስምምነት ሲነገራቸዉ እንደማልተስማሙ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን አሰባስበን ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን፡፡
አላሁ አክበር!

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s