የኢሕአግ ሰራዊት በዋልድባ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከወያኔው የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈጸምኩ ሲል ለዘ-ሐበሻ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።
የድርጅቱ ጋዜጣዉ መግለጫ “ የግንባሩ ሰራዊት በዋልድባ ልዩ ስሙ ሰቋር በተባለ ቦታ በሚያዚያ 8-2005 ዓ.ም የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መመኪያ በሆነው የፈጥኖ ደራሽ ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 25 አቁስያለሁ; ካለ በኋላ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያ መካሄዱንና  በዚሁ እለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት 25 የወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል የተቀዳጀ መቀዳጀቱን ጠቅሶ  በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አትቷል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረጋቸው አውደ-ውጊያዎች ላይ በድምሩ 46 የፈጥኖ ደራሾችን ከጥቅም ውጭ በማድረግና 64 በማቁሰል የግንባሩ ሰራዊት የተሰለፈበትን ሐገራዊ ተልዕኮውን በመፈፀም በጠላት ላይ ከፍተኛ የሕይወትና የንብረት ኪሳራ በማድረስ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል። ያለው የድርጅቱ መግለጫ የግንባሩ ሰራዊት ጥቃቱን በፈፀመበት አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ስርዓቱ በሚያራምደው የግፍ አገዛዝ ከፍተኛ ምሬትና ተቃውሞ በማሰማት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትም የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በማበርከት ሐገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ግንባሩ ሰራዊት እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ሲል ጋዜጣዊ መግለጫውን አጠናቋል።
የአርበኞች ግንባር በበተነው ጋዜጣዊ መግለጫ ዙሪያ የኢሕአዴግ መንግስት የሚሰጠውን ምላሽ ለማካተት ያደርገነው ጥረት ባይሳካም፤ እስካሁን በይፋ የሰጠው ምላሽም የለም።

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s