የግራዚያኒ ሀውልት እንዲሰራ ፈቃድ የሰጡት ከንቲባ እየተመረመሩ ነው

ኢሳት ዜና:-በሮም ደቡባዊ ግዛት የምትገኘው ቲቮሊ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ኢርኮሊ ቪሊ  የህዝብን ገንዘብ በአለም በወንጀለኛነቱ ለተፈረጀው ሮዶልፎ ግራዚያኒ ሀውልት ማሰሪያ በመጠቀማቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አንሳ የተባለው ድረገጽ ዘግቧል።

ሀውልት እንዲቆም የተወሰነው አንድ ማንነቱ ላልታወቀ ወታደር ቢሆንም ፣ ከንቲባው ግን በኢትዮጵያ እና በሊቢያ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎችን ላካሄደው ግራዚያኒ እንዲሆን ማድረጉ ለምርመራ መጋበዙን ድረገጹ ጠቅሷል።

ድረገጹ የላዚዮ ግዛት ባለስልጣናት ፈንዱን ለግራዚያኒ ሀውልት ማሰሪያ ለምን እንደፈቀዱም ምርመራ እንደሚደረግባቸው ዘግቧል።

የግራዚያኒ ሀውልት ስራ የመላው ኢትዮጵያውያንን ቁጣ መቀስቀሱ ይታወቃል።

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s