ማመልከቻ፤ ኢህአዴግ እንድትታሰር ስለመጠየቅ

eprdf-logo

 

እኔ አመልካች ስሜ ከበስተመጨረሻ ባይገለፅም ግድ የለም፤ የማመለክተው ፍሬ ሀሳብ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ኢህአዴግ የተባለች የአራት ጥምር ፓርቲዎች ግንባር እንዳለች ይታወቃል፡፡ ግንባሯ ስሟ ግንባር ሲሏት ትንሽ ትመስላለች እንጂ በተለይ ሀብት ንብረቷን እንቁጠረው ብንል ማለቂያም የለው እና ግንባር ብቻ ሳትሆን ፊት፤ ፊት ብቻም ሳትሆን ጀርባ፤ ጀርባ ብቻም ሳትሆን ዳሌ ናት እንጂ ግንባር የሚለው ብቻ አይበቃትም፡፡ (በቅንፍም ለወደፊትም “ኢህአዴግ” የሚለው ስሟ አይስተካከላትምና  ”ኢህአዴዳ” ብትባል የሚል ሀሳብም አለኝ)

ለማንኛውም ግንባሪቱ፤ የሞጃዎች ሞጃ፤ የባለጠጎች ባለጠጋ፤ የቱጃሮት ቱጃር ናት፡፡

ይቺ ግንባር ቀድሞ ምንም ያልነበራት እና ምንም ያልነበረች ብትሆንም ከዕለት ዕለት ግን ብልጥግናዋ አለቅጥ… እየሰፋ እየሰፋ መጥቶ ከሀገሪቱ በላይ የግንባሪቱ ሀብት ሰማይ ነክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ጸረ ሙስና እና ጸረ አለ አግባበብ መበልፀግ፤ ድርጅት ተቋቁሞ በርካታ የኢህአዴግ ልጆችን ወደ እስር ቤት ማውረዱን አመልካቹን ግለሰብ ጮቤ ያስረገጠ መሆኑን አስረግጬ መናገር እወዳለሁ፡፡ ነገር ግን ለዛሬ ይህንን ማመልከቻ እንድፅፍ ያስገደደኝ ሀሳብ በአዲስ መስመር የሚገኘው ነው፤

እንኳንስ ጸረ ሙስና ያኽል ድርጅት ይቅርና፤ ማንም ድርጅት ያልሆነ ግለሰብ እንደሚረዳው አንድ ህመም ከስሩ እስካልታከመ ድረስ መፍትሄ አያገኝም፡፡ የኢህአዴግ ልጆች የያዛቸው ይሄ ሙስና የተባለ ደዌ መነሻው ከቤተሰብ ነው፡፡ ታድያ ዋናው የቤተሰቡ ሃላፊ በደዌው እየተሰቃየ ሳለ ልጆቹን ብቻ ለህክምና መውሰድ ዘላቂ ብልሃት ነውን… ብለን የጠየቅን እንደሆነ መልሱ የለም የሚል ይሆናል፡፡

ግንባር ኢህአዴግ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ በርካታ ሀብት አፍርታለች ይህም በሙስና ደዌ መጠቃቷን የሚያሳይ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

ስለሆነም ራሷ የቤተሰቡ ሃላፊ የሆነችው ኢህአዴግ እንድትታሰር፤ በዛም በእስር ከሚገኙ ልጆቿ ጋር ህክምና አግኝታ እንደ ቀደመው ልጇ አቶ ታምራት ላይኔ፤ ስኳር በዞረበት የማትዞር አላግባብ ብልጽግና በዞረበት የማትዞር፣ በሰራችው የምትፀፀት እና ይቅርታ ጠያቂ እንድትሆን ትደረግ ዘንድ በማክበር እጠይቃለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር!

ኢትዮጵያ ትቅደም!

Abe Tokichaw

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s