የወያኔ ፖሊስ አባል 12 ንጹሃን ዜጎችን ባህርዳር ላይ ረሸነ

(ዘ-ሐበሻ) በባህር ዳር ከተማ ልዩ ስሙ አባይ ማዶ በተባለ አካባቢ አንድ የወያኔ ፖሊስ አባል 12 ሰዎችን ገደለ፤ የመንግስት ሚዲያዎች ፖሊሱ ሰክሮ ነበር በሚል ዜናውን ለማለዘብ ቢሞክሩም አስተያየት ሰጪዎች ግን ጉዳዩን በጥርጣሬ እየተመለከቱት ነው።

 

የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደረጀ አቻምየለህ “ግለሰቡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በመንገድ ላይ በከፈተው ተኩስ ከሞቱት 12 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል።” ካሉ በኋላ ገዳዩን የወያኔ ፖሊስ አባል ክትትል በማድረግ ልንይዘው ብንሞክርም ራሱን ወንዝ ውስጥ በመወርወር ሕይወቱን አጥፍቷል በማለት ተናግረዋል።

 

ይህ የወያኔ ፖሊስ አባል በትናንትናው ዕለት 12ቱን ንጹሃን ዜጎች ሲረሽን ከሟቾቹ ውስጥ ሴቶች ፣ ህፃናትና አዛውንቶች እንደሚገኙበት ሲታወቅ ፖሊሱ ይህን ወንጀል ለምን ሊፈጽም እንደቻለ የታወቀ ነገር አለመኖሩን መርማሪዎች አስታውቀዋል።

 

ትናንት ከተገደሉት ግለሰቦች መካከልም የአስከሬን ምርመራና ሌሎች ምርመራዎች በደንብ ሳይጠናቀቁ በጥድፊያ የሰባቱ የቀብር ስነ ስርዓት በአንድ ላይ በአስቸኳይ ዛሬውኑ እንዲፈጸም መደረጉና ከግድያው በስተጀርባ ያሉት ጉዳዮች ከወዲሁ አነጋጋሪ ሆነዋል።

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s