የባህር ዳር እጣን መጋዘን ተቃጠለ!

በባህር ዳር የሚገኘው የጅንአድ የእጣን ማከማቻ መጋዘን ተቃጠለ፡፡ እሳቱን ለማጥፋት ከአየር ሀይል፤ ከአድማ ብተናና ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጡ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየነደደ ያለውን መጋዘን ለማዳን እየተረባረቡ ቢሆንም የእጣኑ መጋዘን ነዲድ እየጨመረ ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡

Fire in bahrdar;  May 21,13

Fire in bahrdar; May 21,13

የተቀጣጠለው መጋዘን በውስጥ በኩል እየነደደ በመሆኑ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ወደ ትልቁና ወደ ዘይት ማከማቻው ሊዛመት ይችላል በሚል ተሰግቷል፡፡ የከተማዋ ነዋሪ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የቃጠሎውን ምክንያት ለማጣራት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ የባህር ዳር ጅንአድ በአገሪቱ ካሉ ጅንአዶች ከ10 ትልልቆች አንዱ ነው፡፡
በሌላ በኩል፤ ባለፈው ሳምንት የፌዴራል ፖሊስ ሰላማዊ ህዝብ መጨረሱ፤ ከዚያም ተከትሎ ከአስር ሰው በላይ የጫነች ጀልባ ጣና ሃይቅ ላይ ሰጥማ በውስጡ የነበሩት ሰዎች ማለቃቸው የቅርብ ጊዜ ዜናዎች ነበሩ። ይህ ሃዘን የከተማውን ድባብ አጨልሞት እያለ፤ አሁን ደግሞ የእጣን ማከማቸው መቃጠል ብዙዎችን የከተማው ነዋሪ እያነጋገረ ይገኛል።

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s