የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሸናፊ እጅጉን አሰናበተ፤ ም/ል ፕሬዚዳንቱ ራሳቸውን አሰናበቱ

አሸናፊ እጅጉ

አሸናፊ እጅጉ

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሰሞኑን ብሔራዊ ቡድኑ ላይ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ ውይይት ለማድረግ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት እየተወያየ ሲሆን በብራዚል አስተናጋጅነት በአውሮፓውያኑ 2014 ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታዎችን በማድረግ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ቢጫ የተሠጠው ተጫዋች ማሰለፉን ተከትሎ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ( ፊፋ ) ማጣራት እያደረገ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ 3ለ0 እንደተሸነፈች እና 3 ነጥብ እንደሚቀንስባት ከተገለጸ በኋላ እየተደረገ ባለው የጊዮን ሆቴሉ ጉባኤ አቶ አሸናፊ እጅጉን ከጸሐፊነት ከኃላፊነታቸው ማንሳቱ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል።

ፌዴሬሽኑም ዋልያዎቹ ሰኔ አንድ ቀን 2005 ዓ.ም ሎባትሴ ላይ ከቦትስዋና አቻው ጋር ባደረጉት ጨዋታ ደቡብ አፍሪካና አዲስ አበባ ላይ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ሁለት ቢጫ የማስጠንቀቂያ ካርድ የተመለከተውና አስራ አራት ቁጥር መለያ ለባሹ ምንያህል ተሾመ መሰለፉ ተገቢ አለመሆኑን ከማመኑም በላይ ለውድድሩ አዘጋጅ ይግባኝ እንደማይጠይቅ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን ይህንን የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተከትሎ ፊፋ ኢትዮጵያ ከቦትስዋና ጋር ያደረገችውን የመልስ ጨዋታ ለባለሜዳዋ ቦትስዋና ፎርፌ እንደሚሰጥና ፌዴሬሽኑም ስድስት ሺ የስዊዝ ፍራንክ ቅጣት እንደሚጥልበት ይጠበቃል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ «ችግሩን ፈጥረዋል» ያላቸውን አካላት በደረጃ ከማሳወቁም በላይ እርምጃ ወስዶ ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ በገለጸው መሠረት ነው አቶ አሸናፊ እጅጉን ያሰናበተው።  በተጨማሪም እየተካሄደ ባለው ጉባኤ  የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ብርሀኑ ከበደ ራሳቸውን ከኃላፊነት ሲያነሱ ሥራ አስፈፃሚውም የአቶ ብርሃኑን ውሳኔ እንዳጸደቀላቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።

Ethiopia national team

Source: http://www.zehabesha.com

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s