በሸህ ኑሩ ግድያ ላይ የመንግስትን ተሳትፎ የሚያረጋግጡ መረጃዎች እየወጡ ነው

ከዚህ በፊት በወጡ መረጃዎች ሸህ ኑሩ ግድያ ላይ የመንግስት ተሳትፎ ለመኖሩ አመላካች ሆኑ መረጃዎች መለቀቃቸው የሚታወስ ነው።

ከነዚህም መካከል፡-

1. የአካባቢው መብራት በደሴ ውስጥ ካሉ አካባቢዎች በብቸኝነት እንዲጠፋ መደረጉና አካባቢው [ግድያው የተፈጸመበት ቦታ] በጨለማ እንዲዋጥ መደረጉ።

2. ከዚህ በፊት መስጂድ ውስጥ በተደረገ ተቃውሞ ሰበብ ከየ ሱቃቸውና ስራ ቦታቸው አካባቢ ተለቅመው የታሰሩት ወንድሞች ፖሊስ ጣቢያ ከደረሱ በኋላ ምርመራ ሲደረግባቸው መስጂድ ውስጥ ተቃውሞ አድርጋችኋል፣ ህዝብን ለተቃውሞ አነሳስታችኋል…ምናምን ሳይሆን “ሸህ ኑሩን ለመግደል አሲራችኋል” በሚል መቀየሩና የታሰሩበትን ምክኒያትና የተመረመሩበት ሂደት አለመገናኘት በወቅቱ ብዙዎችን (ተጠርጣሪዎቹን ጭምር) ግራ ያጋባ ነበር። መንግስት ሸህ ኑሩን ሊገድል እንዳሰበና ለዚህም ወንጀሉ ሽፋን ቀድሞ በህዝቡ መካከል ለመርጨት ያደረገው እንቅስቃሴ እንደሆነ ህዝቡ እንዲገነዘብ አድርጓል።

3. ግድያውን የፈጸመው አካል ግድያውን የፈጸመበት ቦታ (ከመኖሪያ ቤታቸው ፊት ለፊት መሆኑ)፣ የግድያው አፈጻጸም (ጥይቱ የመታቸው ለኢላማ የሚከብዱ የሰውነት ክፍሎች (ግንባር፣ አንገትና ደረት) መሆናቸው የግለሰቡን የሰላ የተኩስ ልምድ ስለሚያመላክት)፣ ገዳይ የተሰወረበት ሂደት (ግድያው ከተፈጸመበት ቦታ አካባቢ ለመደበቅ የሚመች ቦታ የነበረ ቢሆንም ገዳይ የሄደው ግን ወደ ከተማው እንብርት መሆኑ ሊይዘው የሚችል አካል እንደሌለ እርግጠኛ ቢሆን እንጂ የመያዝ ስጋት ያለበት በተቃራኒው አቅጣጫ መሸሽ ይችል ስለነበር) ወ.ዘ.ተ

4. ግድያው በተፈጸመበት ቦታ የመንግስታዊ-ሀይማኖት (አህባሽ) አስፈጻሚዎች የሚሄዱበት በመሆኑ መንግስት ጥበቃ ለማድረግ ሲል ለረጅም ጊዜያት መድቦ የሚያስቀምጣቸው ሚኒሻና የፖሊስ ሀይሎች በዚያን ቀንና ሰዓት በቦታው አለመኖራቸው ከመረጃዎቹ አንዱ ነው። እነዚህን ግለሰቦች የሚያዛቸው የደህንነቱና የመንግስት የፖለቲካ አመራሩ ስለሆነ በቦታውና በሰዓቱ ባለመኖራቸው እስካሁን ባለው የምርመራ ሂደት የጠየቃቸውም ስለሌለ እንዲኖሩ እንዳልተፈለገ አመላካች ነው።

5. መንግስት የቀብሩን ሂደት ያስፈጸመበት ሂደት አንዱ ነው። ግለሰቡ የተገደሉት ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ መሆኑ ይታወቃል። ሆስፒታል ተወስዶ እስኪመለስ ወደ 3፡15 ይሆናል (ቶሎ ስለተመለሰ)። መደናገጡና ወንጀለኛውን የመፈለጉ ሂደት አንድ ትልቅ መሳሪያውን በሞት የተነጠቀ መንግስት ሊያደርገው የሚገባ ሆኖ ሳለ የመንግስት አመራሮቹ ያደረጉት ነገር ቢኖር በየ ወረዳው በመደወል ቀባሪ አንዲሰባሰብ ማድረግ ነበር። ሩቅ ከሚባሉ ወረዳዎች ሁሉ በመንግስት መኪኖችና በኮንትራት መኪኖች ተጭነው የመጡ ግለሰቦች ብዞዎች ነበሩ። ይህ የሚያሳየው የመንግስት አካላት የወሰዱት እርምጃ የገዳይን ዱካ ከማፈላለግ ይልቅ ግድያው ሲፈጸም/ሲታቀድ የታሰበለውን ፖለቲካዊ ግብ የማሳካት ሂደት አጠናክሮ መቀጠል ነበር።

ተጨማሪዎቹ መረጃዎች፡-

6. ሟች ለመንግስት እንደ መሳሪያ በመሆን በህዝበ-ሙስሊሙ ላይ ካደረሰው በደል አኳያ ጥቃት ይፈጸምበታል ብለው የሰጉ የሸዋበር መስጂድ ሊስትሮዎች [የአህባሽ አራማጆች ናቸው] በየቀኑ ከኢሻ ሰላት በኋላ ሸህ ኑሩን አጅበው እቤታቸው ያደርሱ ነበር። በእለቱ እነዚህ አጃቢዎች ከመግሪብ በኋላ “በጁምዓ ሊደረግ ስለሚችል ተቃውሞ ልናናግራችሁ አንፈልጋለን….” በሚል ሀሳብ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መጠራታቸውና ግድያው እስኪፈጸም ድረስ አለመመለሳቸው ነው። የመንግስት አካላት ግድያው ሊፈጸም በሚችልበት ሰኣት አጃቢዎቹ እንዳይኖሩ በመፈለጋቸው ወደ ፖሊስ መምሪያቸው ወስደው አቆይተዋቸዋል።

7. ሌላው ደግሞ የክልሉ የደህንነት ሀላፊ ግድያው በተፈጸመበት እለት በደሴ ከተማ መታየቱ ነው። ይህ ግለሰብ ግድያውን ለማስፈጸምና ግድያው ሂደት ስለሚፈጸምበት አግባብ ለመመካከር እንደመታ ውስጥ አዋቂዎች ጠቁመዋል። እነዚሁ ውስጥ አዋቂዎች እንዳሉት ይህ የደህንነት ሀላፊ አርብ እለት ሌሊት ከደሴ እንደወጣ ተናግረዋል። ይህ የደህንነት ሀላፊ ይህን ግድያ ለማስፈጸም ባይመታ ኖሮ የግድያውን ሂደት ለማታራትና ተጨማሪ ትቃቶች ቢኖሩ እንኳን ለመከታተልና ድጋፍ ለማድረግ መቆየት ይኖርበት ነበር። ነገርግን ስራውን ስለጨረሰ ከሀሙስ ሌሊት ውጭ ደሴ መቆየት ስላላስፈለገው ከደሴ ሊወጣ ችሏል።

ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች የሚያመለክቱት መንግስት በሸህ ኑሩ ግድያ ሂደት ውስጥ ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ነው።

አላህ ሆይ! ጠላቶቻችን የሚሸርቡበትን ሴራ አጋልጥባቸው!! ኡማውን ከሴራቸው ጠብቀው!!! አላማቸውንም አክሽፍባቸው!!!

አሚን!!!

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s