የመድረክ ሕዝባዊ ስብሰባ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

 

ኢሳት ዜና :- የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአደባባይ ላይ ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ሰልፍ ተገዶ ወደ ሕዝባዊ ስብሰባ መቀየሩ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ግንባሩ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ/ም ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገልጿል፡፡

ከወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ከስድስት ኪሎ እስከድላችን ሐውልት ድረስ ሕዝባዊ ሰልፍ ለማካሄድ ግንባሩ መርሃግብር ነድፎ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም የአዲስአበባ ከተማ አስተዳዳር ከተማዋ በተለያዩ ልማቶች የተቆፋፈረች በመሆኑዋ ሰልፉን ለማካሄድ አመቺ አይደለም በሚል ምክንያት ፈቃድ መከልከሉ ታውቋል፡፡መድረክ የአደባባይ ሰልፉን በቤት ውስጥ ስብሰባ በመቀየር በድጋሚ ለአስተዳደሩ እንዲያውቀው ያስገባው ይፋዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ አግኝቶ ስብሰባው በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የመብራት ኃይል አዳራሽ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s