UPDATED NEWS: በአምስት ከተሞች የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁኔታ (የመቐለው ተሰረዘ፤ በሌሎች ከተሞች ሰልፉ ተጀምሯል!)

EMF – በአንድነት ፓርቲ አስተባባሪነት – ዛሬ በመቐለ፣ በባህር ዳር፣ በጅንካ፣ በወላይታ እና በአርባ ምንጭ ሊደረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ ልዩ ልዩ እንከኖች ቢያጋጥሙትም፤ አሁን በባህር ዳር የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የተጀመረ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። በመቐለ ሊደረግ የነበረው ስብሰባ በህወሃት ሰዎች የሃይል እርምጃ ሊደረግ አልቻለም። ህወሃት በስፍራው የተገኙትን የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት አስሯቸዋል። በመሆኑም ስብሰባውን ማድረግ አልተቻለም። በህጋዊ እና በሰለጠነ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የሌላ ፓርቲ ሰዎች ማሰር፤ ያለመሰልጠን አንደኛው ምልክት ሆኖ አልፏል።

በጅንካ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማክሸፍ በሺ የሚቆጠሩ ታጣቂ ሃይሎች የከተማውን ዋና ዋና ጎዳናዎች በመቆጣጠር ህዝቡን እያሸበሩት ቢሆንም፤ ሰላማዊ ሰልፉ ግን በአሁኑ ሰዓት እየተከናወነ ነው። በወላይታ የአመራር አባላቱን አፍኖ ማሰር ብቻ ሳይሆን፤ ከአስተባባሪዎቹ ልጆች አንዱን አፍነው ወስደውታል። በአርባ ምንጭ ቅስቀሳ ሊደረግባት የነበረችው መኪና ጎማዎች ሙሉ ለሙሉ እንዲተነፍስ ቢደረግም ሰላማዊ ሰልፉ ግን እየተከናወነ ነበር። ሆኖም የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ሰልፉ መሃል ገብተው እየበጠበጡ እና አስተባባሪዎቹን “እንገላችኋለን!” በማለት እያስፈራሯቸው ነው – ሌላው ያለመሰልጠን ምልክት!! በወላይታ ሶዶ ህዝቡ የተጠራው ለሰላማዊ ሰልፍ ሳይሆን ለህዝባዊ ስብሰባ ነው። ታጣቂዎች ህዝቡ ወደ ስብሰባ አዳራሽ እንዳይሄድ ቢከለክሉም፤ ህዝቡ ግን፤ “መብቴ ነው!” እያለ ነበር ወደ አዳራሹ እየጎረፈ የሄደው። ለዚህም ነው፤ ስብሰባው በተጀመረበት ወቅት ሰብሳቢው፤ ህዝቡን “ጀኖች ናቹህ! ጀግኖች ናቹህ!” በማለት ንግግግራቸውን የጀመሩት። በወላይታ ሶዶ የታሰሩትን የአንድነት ፓርቲ ተጠሪ ወ/ሮ ሃድያንም በዚህ አጋጣሚ አስታውሰዋል። ስብሰባው ሞቅ ደመቅ ብሎ እንደቀጠለ ነው። በባህርዳር መንግስታዊ ውንብድና እየተከናወነ ይገኛል። በባህር ዳር የመንግስት አካላት አረንጓዴ ሽብር የሚል ወረቀት እየተበተኑ ናቸው። “አረንጓዴ ሽብር” የሚል በነጭ ወረቀት የተባዛ እና የአንድነትን የስልክ ቁጥር የያዘ በራሪ ወረቀት እየተበተነ መሆኑ ታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የበተነው በራሪ ወረቀቶች ቢጫና ቀይ ብቻ መሆኑ ይታወቃል፡፡

አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር የጠራው ሰላማዊ የተዋውሞ ሰልፍ በድምቀት እየተጠናቀቀ ነው በአሁኑ ሰዓት የምዕራብ ጎጃም የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ንግግር እያደረጉ ነው፡፡

bahrdar

በሁሉም ስፍራዎች እየተደረገ ያለው የኢህአድጋውያን ህገ ወጥ እርምጃ ብስለት እንደሚያንሳቸው ብቻ ሳይሆን ዛሬም አለመሰልጠናቸውን በጉልህ የሚያሳየን መስታወት ሆኗል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አንድነት ፓርቲ ቅስቀሳውን እና ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ሙከራውን እንደቀጠለ ነው። ከላይ እንደገለጽነው፤ ከመቐለው ስብሰባ በቀር በሌሎቹ ከተሞች ከአፋኝ ሃይሎች ጋር እየተፋለሙ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። በጂንካ እየተደረገ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ምንም እንከን ሳያጋጥመው በሰላም በመካሄድ ላይ ይገኛል። bahrdar2 በጂንካና በባህርዳር እየተስተጋቡ ያሉ መፈክሮች በከፊል ========================================== • የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ • መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር • መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም! • መንግስት ለብሄራዊ መግባባት ባስቸኳይ መልስ ይስጥ! • ውሸት ሰልችቶናል! ይቁም!!! • የጸረ – ሽብር ህጉ ባስቸኳይ ይሰረዝ! • ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቁም!! • ሙወስና የስርአቱ መገለጫ ነው!! • የአባይ ጉዳይ የኢትጵያ ሕዝብ ነው! • ለተከሰተው የኑሮ ውድነት ተጠያቂው መንግስት ነው!! • የዜጎች ሰብአዊ መብታቸውን የማግኘት መብታቸው ይከበር!! • ዜጎች በሀገራቸው ስራ የማግኘት መብታቸው ይከበር!! • በአባይ ጉዳይ ወሳኙ የኢትጵያ ሕዝብ እንጂ ግብጾች ይደሉም!! • የፓርቲ አባልነት በፍላጎት መሆን አለበት!!

 

ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ነው፡፡ (Photo source: Abugida)

ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ነው፡፡ (Photo source: Abugida)

 

በመቐለ ሰላማዊ ሰልፉ ለአሁኑ ይሰረዝ እንጂ ወደፊት የሚደረግ መሆኑን ፓርቲው አሳውቋል። በአሁኑ ወቅት የአመራሩ መታሰር ብቻ ሳይሆን ንብረታቸው በታጣቂዎች መዘረፉም በጣም የሚያሳዝን ነው። ከምንም በላይ ግን፤ “ለመብት እና ለነጻነት ታግለናል” የሚሉት ህወሃቶች እንዲህ ያለ ድርጊት መፈጸማቸው አሳፋሪም ጭምር ነው። አብርሃ ደስታ በቁጭት ካስተላለፈው መልዕክት መሃል ይሄንን እናስነብባቹህ። እንዲህ አለ… “በትግራይ ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የደርግን አገዛዝ ለመጣል ብዙ መስዋእት ከፍሏል። መሰረተ ሓሳቡ: ብዙ መስዋእት የከፈለ ህዝብ ብዙ ዓፈና ይደርሰዋል። ስለዚህም ብዙ መስዋእት የከፈለ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጓል። በሌሎች ክልሎች ቢያንስ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ እየወጣ ነው። በትግራይ ግን ሰልፍ መውጣት ከድሮ ጀምሮ ወንጀል ተደርጎ ይወሰዳል። ይሄው እስካሁን ድረስ አለ። አዎ! ብዙ መስዋእት የከፈለ ብዙ ጭቆና ይደርሰዋል። ብዙ መስዋእት ለብዙ ጭቆና!” በሚል ስላቅ አዘል አጻጻፍ ነው የትግራይን ህዝብ አፈና የገለጸው።

እስካሁን እየተደረገ ያለውን የክልሎች ሁኔታ ስንመለከት… በትግራይ የዲሞክራሲ ስርአቱ ጨርሶ የሞተ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል። ባህር ዳር ሻል ያለ ነው። በወላይታ እና በአርባ ምንጭ የተደረገውን ያልሰለጠኑ ሰዎች ትንኮሳ፤ ከጅንካው ሁኔታ ጋር ስናነጻጽረው፤ የጅንካ ህዝብ የተሻለ ስልጡንን ሆኖ አግኝተነዋል።

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s