ቀጣዩ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ማን ይሆኑ?

 

       

ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን ይሆኑ?      ዋና ዜና       
25 August 2013         ተጻፈ በ         

  ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን ይሆኑ?  

  

    

                

ኢትዮጵያን ላለፉት 12 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሁለተኛው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የሥራ ዘመናቸው በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡

  

በመሆኑም ከአንድ በኋላ ወር በመስከረም 2006 ዓ.ም. ማጠናቀቂያ አካባቢ ሦስተኛው ፕሬዚዳንት ይሰየማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሦስተኛው ፕሬዚዳንት ማን ሊሆኑ ይችላሉ? ወይም ይገመታሉ? ለሚሉ ጥያቄዎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ግምታቸውንና በመረጣ ወቅት ምን መደረግ እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሦስተኛውን ፕሬዚዳንት በሚቀጥለው ወር ይፋ ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል የፕሬዚዳንትነቱ የሥራ ኃላፊነት ያን ያህል ትርጉም ስለሌለው እንደማያስጨንቃቸው የሚናገሩም አሉ፡፡ የመጀመሪያው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በ1987 ዓ.ም. በተደረገው የፓርላማ ምርጫ ተወዳድረው ከተመረጡ በኋላ፣ በወቅቱ የአመራር አባል የነበሩበት ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በደረሱበት ውሳኔ መሠረት ፕሬዚዳንትነታቸው በፓርላማ ፀድቆ፣ እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ከኢሕአዴግ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስከሚለያዩ ድረስ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ቆይተዋል፡፡

ከእሳቸው በመቀጠል በቅርቡ የሚሰናበቱት አቶ ግርማ ላለፉት አሥራ ሁለት ዓመታት ቆይታ አድርገዋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ መሠረት አንድ ፕሬዚዳንት ከዚህ በላይ ስለማይቆይ በአዲሱ ዓመት ሦስተኛው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ይሰየማሉ፡፡ ምንም እንኳ ኢሕአዴግ ቀደም ብሎ ለሕዝቡ የማሳወቅ ባህል ባይኖረውም፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ የተለያዩ ግለሰቦች ስሞች እየተነሱ ናቸው፡፡ ለፕሬዚዳንትነት በዕጩነት ስማቸው የሚነሱ ግለሰቦችንና የተሰጡ አስተያየቶችን የያዘው ዝርዝር ዘገባ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡ 

ethiopianreporter.com

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s