ኢህአዴግ ልማቱን ለመጨረስ ከ40 እስከ 45 አመት ያስፈልገዋል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

 ኢሳት ዜና :-የጠ/ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት ለኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ነው። ለማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን ዝግ በሆነው የካድሬዎች ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ወረቀታቸውን ያቀረቡት አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ የህዝቡን የነፍሰ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ  ቢያንስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።

አቶ በረከት የወደፊቱ የህዳሴ መንገድ በሚል ባቀረቡት ጽሁፍ ፣ ግንባሩ የኢትዮጵያ ህዳሴ በስንት ዓመታት ሊጠቃለል ይችላል የሚለውን ከእነኮሪያና ታይዋን ልምድ በመውሰድ መስራቱን ተናግረዋል። አገሮች ከዝቅተኛ ወደ መካከለኛ ከዚያም ወደ ከፍተኛ ገቢ ለመድረስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት መውሰዳቸውን ገልጸዋል ።

አቶ በረከት መካከለኛ ገቢ የሚባለው ከገቢ አንጻር ሲሰላ ዝቀተኛው 1000 ዶላር ከፍተኛው ደግሞ 5 ሺ ዶላር መሆኑን ጠቅሰዋል። ባለፈው 10 አመታት የጀመርነውን እድገት ከቀጠልን በሚቀጥሉት 10 አመታት የመካከለኛው ገቢ ዝቀተኛ ጣራ ከሆነው 1000 ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ደረጃ ላይ እንደርሳለን የሚሉት አቶ በረከት፣ የመካከለኛ ገቢ ከፍተኛ ጣራ ከሆነው 5 ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ለመድረስ እንደገና ተጨማሪ 15 ወይም 20 አመታት ይወስድብናል ብለዋል;፡

የከፍተኛው ገቢ የመጨረሻው ደረጃ ለሆነው የ10 ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ደረጃ ለመድረስ ሌላ ከ15-20  ተጨማሪ አመታት እንደሚያስፈልግ አቶ በረከት አክለዋል። ይህንን ጊዜ ለማሳጠር ብንፈልግ ልናሳጥረው አንችልም የሚሉት አቶ በረከት ፣ እድገቱ አንዳንዴም ልክ ቱኒዚያ፣ ታይላንዳና ማሌዢያ እንደተቋረጠባቸው ሊቋረጥ ይችላል ብለዋል።

ይህን እደገት ለማስቀጠል ፈተናዎች አሉ ያሉት አቶ በረከት፣ አንደኛው ፈተና  እድገቱን ህብረተሰቡ ሳይሰለች ማስቀጠል ይችላል ወይ  የሚለው ነው ሰሉ ተናግረዋል።

“ነባሩ አመራር  በእድሜ፣ በጤናና በመድከም ከሃላፊነት የሚወጣ በመሆኑ አዲሱ ትውልድ በተመሳሳይ ትኩረትና ፍጥነት እድገቱን ይዞት ሊሄድ ይችላል ወይ?’ የሚለው ጥያቄ ያልተመለሰና መመለስ ያለበት ነው ሲሉ ኢህአዴግ ያጋጠመውን ፈተና ገልጸዋል። ኢሳት የድምጽ መልእክቶችን በመላክ የሚተባበሩንን ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች ለማመስገን ይወዳል።

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s