የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ

 

አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ

one two

                      

ክፍል አንድ

ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫ ስለሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ የሚኖረውን ገጽታ እና ትርጓሜ ማስቀመጥ ያስቸግራል። አንዱ ሰው የሚፈራውን ነገር ሌላው ላይፈራው ስለሚችል ፍርሃት እንደ የግለሰቡ ባህሪ እና ጥንካሬ ወይም ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ የተለያየ መልክ ይኖረዋል። ይሁንና በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የሚጋሩት ባህልና ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ እንደመኖሩ ሁሉ የሚጋሩትም ፍርሃት ወይም ደስታ ወይም ሃዘን ወይም ድፍረት ወይም ሌሎች ባህሪያት ይኖራል። በዚህም ምክንያት አንዳንድ ሰዋዊ ባህሪያት ለአንድ ማህበረሰብ ወይም ለበርካታ ሰዎች የወል መገለጫ ተደርጎ ሲገለጽ ይስተዋላል። ‘የዚህ አካባቢ ሰዎች ጀግኖች ወይም ጸብ ፈሪዎች ወይም እሩህ ሩህዎች ወይም ጨካኞች ወይም ቂመኞች ወይም ገራገሮች ወይም ተንኮለኖች ወይም ጎጠኞች ወይም ሌላ ባህሪ ያላቸው ናቸው’ የሚል አገላለጽ የተለመደ ነው። ይህ አይነቱ አነጋገር ሳይንሳዊ መሰረት ያለው ባይሆንም በአካባቢው ላይ ጎላ ብለው በሚታዩ ሰዎች ላይ ተደጋግሞና ተዘውትረው የሚታዩ ተመሳሳይ ባህሪያት የአካባቢው ሰው ሁሉ መገለጫ ተደርገው ስለሚወሰዱ ድምዳሜው ለስህተት የተጋለጠ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ለመግለጽ እወዳለሁ። ከዚህ መንደርደሪያ በመነሳት በዚህ ጥልቅ ጥናት ባላካሄድኩበት ነገር ግን ደጋግሜ ሳብሰለስለው በቆየሁት የፍርሃት ባህል እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድባብ ዙሪያ ያለኝን ምልከታ ለአንባቢያን ለማካፈልና በጉዳዩም ላይ ለመወያየት ወሰንኩ።

በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የፍርሃት ድባብ እንዲሰፍን እና ከዚያም አልፎ ባህል እንዲሆን ምክንያት ከሆኑት በርካታ ነገሮች መካከል የተወሰኑትን ልጥቀስና በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ገጽታ በመጠኑ ለመዳሰስ እሞክራለሁ። በስነ-ልቦና ጠበብቶች ከሚጠቀሱት ዋና ዋና የፍርሃት ምንጮች መካከል፤ ነፃነትን ማጣት፣ ነገ የሚሆነውን ማወቅ አለመቻል፣ የህሊና እና የአካል ቁስልን ባስከተሉ ትላንቶች ውስጥ ማለፍ፣ የማያቋርጥ ብስጭት ወይም ንዴት፣ ድህነት በሚያስከትለው ስቃይ ውስጥ መማቀቅ፣ አጋር እና አለኝታ ማጣት፣ በሌሎች ክፉኛ መነቀፍ፣ መንጓጠጥ፣ መጠላት እና መገለል፣ በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ዘንድ ተቀባይነትን ማጣት፣ የሞት አደጋን ማሰብ፣ ሽንፈት ወይም ስኬት አልባ ሆኖ መቆየት፣ እና ሌሎችም ይገኙበታል። ከእነኝህ መክንያቶች ውስጥ የአንዱ መከሰት አንድን ሰው ወደ ፍርሃት ውስጥ ሊከት እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ። እነኝህ ምክንያቶች ተደራርበውና በአንድ ጊዜ በአንድ ሰው ወይም በአንድ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ሲከሰቱና ዕልባት ሳያገኙ እረዘም ላለ ጊዜ ሲቆዩ ደግሞ አደጋቸው የከፋ ነው የሚሆነው። ከዚህም በመነሳት ወደ እኛ ማህበረሰ ስንመለስ በግላችንም ሆነ በጋራ ህይወታችን ከላይ ከተጠቀሱት የፍርሃት መንሰዔዎች መካከል ስንቶቹ በህይወታችን ውስጥ ተከስተዋል፣ ስንቶቹን በአሸናፊነት አለፍናቸዋል፣ ስንቶቹስ ዛሬም ድረስ አብረውን ይኖራሉ፤ የሚሊቱን ጥያቄዎች እያንዳንዱ ሰው እራሱን እንዲጠይቅ እየተውኩ በወል በምንጋራቸው ጥቂት የፍርሃት መንሰዔዎች ላይ ላተኩር።

የነፃነት ማጣት

ሰብአዊ መብቶች በገፍ በሚጣሱበት እና ዜጎች የሰውነት ክብራቸው ተገፎ፣ ተዋርደውና ነፃነታቸውን ተነጥቀው በሚኖሩበት አገር ሁሉ ፍርሃት ትልቁ ገዢ ኃይል ነው። በእንዲህ ያለው ማህበረሰብ ውስጥ የፍርሃት ሰለባ የሆኑት እና ነፃነት አልባ ሕይወትን የሚገፉት ተጨቋኞቹ ብቻ ሳይሆኑ ጨቋኞቹም ጭምር ናቸው። ተጨቋኖቹ በግፍ ልንገደል፣ ልንታሰር፣ የስቃይ ሰለባ ልንሆን፣ ታፍነን ልንሰወር፣ ከሃገር ልንሰደድ፣ ከሥራ ልንባረር፣ ንብረታችን ሊወረስ፣ በግዞት ከቦታ ቦታ ልንዛወር፣ ከቅያችን ልንፈናቀል፣ በሃሰት ክስ ልንወነጀል፣ ደሞዛችንን ልንነጠቅ፣ ከሥራ ደረጃችን ልንቀነስ፣ ወዘት … እያሉ አደጋዎችን እያሰቡ በሽብርና በፍርሃት ቆፈን ተይዘው ‘ጎመን በጤና’ በሚል የማፈግፈጊያ ስልት መብቶቻቸውን አሳልፈው በመስጠት የግፍ እንቆቋቸውን እየተጎነጩ መራራ ሕይወታቸውን ይመራሉ። ጨቋኞቹም ይህን በነፍጥ እና በሕግ አንበርክከው ነፃነቱን የነጠቁትና ለስቃይ የዳረጉት ሕዝብ በአንድ አይነት ተአምር በቁጣ ገንፍሎ ከተነሳ አንድም ቀን እንደማያሳድራቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ እያንዳንዱን ደቂቃና ሰዓታት ልክ እንደ ተጨቋኙ በፍርሃት እና በሽብር ነው የሚያሳልፉት። ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱም፣ የእለት ሥራቸውንም ሲያከናውኑ፣ ሲተኙም ሆነ ሲዝናኑ በሠራዊትና በመሣሪያዎች ጋጋታ ታጅበው ነው። ምናልባትም ከተጨቋኞቹም በባሰ ፍርሃት ውስጥ ነው የሚኖሩት።

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በቅጡ ያጤንን እንደሆነ ገዢና ተገዢ እርስ በእርስ የሚፈራሩበት፤ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ተቃዋሚዎች መንግሥትን የሚፈሩበትና አንዱ ሌላውን የማያምንበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። የመንግሥት ፍርሃት ከተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች አልፎ የሲቪክ ማኅበረሰቡን፣ የሙያ ማኅበራትን፣ ነጋዴውን፣ ምሁራኑን፣ ገበሬውን፣ ወጣቱን እና ሌላውንም የኅብረተሰብ ክፍል ክፉኛ የሚፈራበትና በቁራኛ የሚከታተልበት፤ እነሱም መንግስትን እንደ ተናካሽ አውሬ የሚፈሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በመንግሥትና በሕዝቡ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በመንግሥት፣ በሕዝቡና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ካለመተማመን የመነጨው ይህ ጥልቅ ፍርሃት በአገሪቱ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ጥቁር ደመናን ጋርዷል። በገዢው ኃይል በኩል ያለውን የፍርሃት ድባብ ለመመልከት በየጊዜው መንግሥት የሚወስዳቸውን የኃይል እርምጃዎች፣ የሚያወጣቸውን የማፈኛ ሕጎች፣ እያጠናከረ የሄደውን የሥለላና የአፈና መዋቅር፣ በመገናኛ ብዙሃን የሚያሰራጫቸውን ሕግን ያልተከተሉ እና በሽብር መንፈስ የተዋጡ መግለጫና ዘገባዎችን መመልከት በቂ ነው። በተለይም የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ ያስደነበረው የወያኔ መንግሥት ከላይ የጠቀስኳቸውን እና አጥብቆ የሚፈራቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ቀፍድዶ ለመያዝና እንቅስቃሴዎቻቸውን ለመገደብ ባወጣቸው የጸረ-ሽብር፣ የሲቪክ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መተዳደሪያ፣ የፕሬስ እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምዝገባ፣ የፀረ-ሙስና እና ሌሎች አዋጆች ሥርዓቱ የአፈና  እና የመብት እረገጣ ተግባሩን ሕጋዊ ወደማድረግ ሂደት የተሸጋገረ መሆኑን ያሳያሉ። ፍጹም ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መልኩ የመብት ጥያቄዎችን ባነሱ ዜጎች ላይ፤ አቅመ ደካሞችን እንኳን ሳይለይ ‘የፈሪ በትሩን’ ሲያሳርፍ በተደጋጋሚ ተስተውሏል።

ባለፉት ሃያ አመታት የአገዛዝ ሥርዓቱ የፈሪ በትሩን በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ አሳርፏል። ብዕርና ወረቀት በያዙ ከከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ አንደኛ ደረጃ ትመህርት ቤት ሕፃናት ጋር ሳይቀር በተደጋጋሚ ጊዜያት ተላትሟል። በርካቶችን ገድሏል፣ አስሮ አሰቃይቷል፣ ደብድቧል፣ ከትምህርት ገበታቸው ላይ አፈናቅሏል፣ ከአገር አሰድዷል፣ በሃሰት ወንጅሎ አስፈርዷል። በእምነት ቤቶች ውስጥ ገብቶ ከአማኞች፣ ከመንፈሳዊ አባቶች እና ይህን አለም ሸሽተው በገዳም ከከተሙ መነኮሳት ጋር ሳይቀር ተላትሟል። የኃይማኖት ተቋማት እንዲከፋፈሉና በገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ተሿሚዎች ቁጥጥር ስር እንዲወድቁ ተደርገዋል። ምእመናን በመስጊዶችና በቤተክርስቲያን ውስጥ እያሉ በታጠቁ ኃይሎች ተገድለዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተዋርደዋል። ቀሳውስት ጥምጥማቸውን እንዲያወልቁ እና መስቀላቸውን እንዲጥሉ ተደርጎ በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የማሰቃየት ተግባር ተፈጽሞቻቸውል። ኢማሞች ጺማቸው እየተጎተተ ተወስደው ተደብድበዋል፣ ታስረዋል። ይህ ሕዝብን የማዋረድ እና የማሸበር ተግባር የመነጨው እንደ እኔ እምነት የገዢው ኃይል እየተባባሰበት ከመጣው የፍርሃት እና የመሸበር ስሜት የተነሳ በራስ የመተማመን ስሜቱ እየተቦረቦረ በመሄዱ ነው። ዛሬ ሥርዓቱ የገዛ ጥላውንም የሚፈራበት፣ አባላቱ ላይ እንኳን እምነት ያጣበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ለእዚህም አንዱ ማሳያው በነጋ በጠባ ቁጥር ማቆሚያ በሌለው የግምገማ ስብሰባ አባላቱን ሲያስጨንቅ መታየቱ እና ለዚሁ የሚያባክነው ጌዜ እና የሕዝብ ገንዘብ፣ የባለሥልጣናት ተደጋጋሚ  ሹም ሽር እና ከአገር ከድተው የሚወጡ ባለሥልጣናት እና የወያኔ አባላት ቁጥር መጨመሩ ነው።

ይህ የገዢው ኃይል የሕግን ልጓም በመበጣጠስ የፈረጠመ ክንዱን ይቀናቀኑኛል ባላቸው ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ኃይሎችና የሙያ ማኅበራትና አባላቶቻቸው ላይ ሁሉ ማሳረፉ ቀሪውን የኅብረተሰብ ክፍል ክፉኛ እንዲደነብርና በፍርሃት ቆፈን እንዲሸማቀቅ አድርጎታል። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች መከበር፣ የዴሞክራሲ ጥያቄዎች እና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ የሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የዕለት ተዕለት ሕይወት የሚነካ ቢሆንም የጥቂቶች ጉዳይ ተደርጎ ተወስዷል። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጥቂት የሲቪክ ማኅበራት፣ ጥቂት ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና በጠአት የሚቆጠሩ ግለሰቦ ብቻ ናቸው ባላቸው ውሱን ጉልበት እና አቅም ሲወያዩ፣ የምንግሥትን መጥፎ ተግባራት ሲቃወሙ፣ ለዜጎች መብት ሲሟገቱ እና ባደባባይ ሲጮሁ የሚስተዋለው።

በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ መቆየት

ሌላው እና ትልቁ የፍርሃት ምንጭ በከፋ ድህነት ውስጥ ለረዥም ጊዜ እየማቀቁ መቆየት እና ድህነቱ ባስከተለው የስቃይ ህይወት አካላዊና መንፈሳው አቅም ተሸርሽሮ ክፉኛ መጎዳት እና መዳከም ነው። ሕዝብን በድህነት ውስጥ አምቆ በማቆየት ለሰው ልጅ ከሚገባው ክብር ወርዶና ከእንስሳ ያልተሻለ ሕይወት እንዲኖር በማድረግ ቅስሙን መስበር የአምባገነኖች አንዱ የሥልጣን እድሜአቸውን ማራዘሚያ ሥልት ነው። የድህነት ክፋቱ ኪስን ብቻ ሳይሆን የሚያራቁተው ክብርንም ጭምር ነው። አንድ ሰው በመንገድ ላይ ቆሞና እራሱን ከመጽዋቾቹ ሥር ዝቅ አድርጎ ቁራሽ ምግብ ወይም ቤሳ ሲለምንና ሲማጸን በኩራትና በደስታ ስሜት ውስጥ ሆኖ አይደለም። እያፈረ እና እየተሸማቀቀ በተሸናፊነትና በዝቅተኝነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ነው። ይህ ክስተት በሙሉ ጤንነት እና በወጣትነት ወይም በጉልምስና እድሜ ላይ ባሉ ሰዎች ውስጥ ሲሆን ደግሞ ያለው የውስጥ ሕመም እና የሕሊና ቁስል እጅግ የከፋ ነው። የድህነት ክፋቱ ያፈሩትን ቅሪት ብቻ ሳይሆን የሚያሳጣው ወይም ኑሮን ለማሸነፍ የሚያስችል አቅምን ብቻ ሳይሆን የሚሸረሽረው መንፋሳዊ ወኔንም ጭምር ነው ከላያችን ገፎ የሚወስደው። ከሰውነት ደረጃ ላይ የሚያቆመንን መንፈሳዊ ልዕልና ካጣን በኋላ ቁሳዊ ድህነቱን ብናሸንፈው እንኳን መንፈሳዊ ድህነቱ ይከተለናል። እዚህ ላይ ለማሳሰብ የምወደው ነገር ድሃ ሁሉ ፈሪ ነው ወይም በፍርሃት ቆፈን የተተበተበ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ እንዳይወሰድ ነው። በከፋ የኢኮኖሚ ድህነት ውስጥ እየኖሩ ክብራቸውን አስጠብቀውና እና በላቀ የመንፈሳዊ ወኔያቸው እራሳቸውንና አገራቸውን አስከብረው ያለፉ ድሃ አያት ቅድመ አያቶቻችንን ማሰብ የግድ ይላል። ዛሬም የገንዘብ እጦትና ድህነት ያላላሸዋቸውና መንፈሳዊ ልዕልናቸውን አስጠብቀው በክብር የሚሞቱ ወገኖች አሉን፤ ትቂቶች ቢሆኑም።

የዚህ ጽሁፍ ትኩረት ግን በቁሳዊውም ሆነ በመንፈሳዊ  ማንነታቸው ውስጥ ድህነትና ፍርሃት ተረባርበው ወይም ከሁለቱ በአንዱ ተጠልፈው ስብእናቸው ፈተና ውስጥ የወደቀባቸውን ሰዎች የሚመለከት ነው። በተለይም በዚህ ግለኝነት በነገሠበት እና ገንዘብ በሚመለክበት የአለም ወቅታዊ  ሁኔታ ውስጥ መናጢ ድሃ ሆኖ ለዘመናት መቆየት መዘዙ ብዙ ነው። ብዙዎች ከዚህ መቋጫው ከጠፋው የድህነት አረንቋ ለማምለጥ ስደትን አማራጭ አድርገው በተለያዩ አቅጣጫዎች አገሪቷን ለቀው ለአረብ አገራት ባርነት ተሰደዋል። ቀሪዎች ደግሞ የአገዛዝ ሥርዓቱ ሎሌ በመሆን ነፃነታቸው በቤሳ መሸቀጥን ቀጥለዋል። ለሁለቱም እድሉን ያጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሆች ደግሞ በየጎዳናው ላይ ተበትነው ዝናብ፣ ውርጭና ፀሃይ እየተፈራረቁባቸው የመጽዋቾቻቸው ደጅ ጠኞች ሆነዋል።

ከተወሰኑ አሥርት አመታት በፊት አንድ ሰው በድህነቱ ምክንያት እራሱንና ልጆቹ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ መሰረታዊ የሆን አልባሳትና መጠለያ ጎጆ ባለቤት ለማድረግ የሚገጥመው ፈተና ቢኖርም ይህን ያህል የመረረ አልነበረም። ዜጎች በወር ከሁለት ብር አንስቶ እንደ የአቅማቸው የቀበሌ እና የኪራይ ቤቶችን ቤቶች ተከራይተው የመጠለያ ችግራቸውን ይቀርፉ ነበር። በአገሪቷ ውስጥ የነበሩ በርካታ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ከመመዝገቢያ ያልዘለለ አነስተኛ ገንዘብ እየተቀበሉ ተማሪዎችን በነጻ ያስተናግዱ ነበር። ብዙ ምሁራንንም አፍርተዋል። በየቀበሌው ከተደራጁ ጤና ጣቢያዎች አንስቶ በተለያዩ የመንግሥት ሆስፒታሎች ዜጎች በነፃና እጅግ ተመጣታኝ በሆነ ክፍያ ጥሩ ሕክምና የማግኘት እድል ነበራቸው። በአንድ ብር በሚገዛው አስር ትንንሽ ዳቦ ወላጆች ልጆቻቸውን አብልተው ያሳድሩ ነበር። ዛሬ አገሪቱ በልማት እየገስገሰች እንደሆነ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ዜጎች በኑሮ ውድነትና ዋስትና ማጣት በጨለማ  ህይወት ውስጥ እየተደናበሩ ይገኛሉ።

መንግሥት በኢኮኖሚውም፣ በፖለቲካውም ሆነ በሌሎች ኃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ያሻውን ቢያደርግ  በሕዝብ በኩል መላሹ ዝምታ ሆኗል። አብዛኛው ሕዝብ ከተዘፈቀበት የድህነት አረንቋ ሳይወጣ በርካታ ነገሮች ተቀይረዋል። በመቶና በሁለት መቶ ይገዛ የነበር ጤፍ በሺዎች ሲያወጣ ምላሹ ዝምታ ሆኗል። ቲማቲም እንኳን ባቅሟ በኪሎ ከሁለት ብር ወደ ሃያ ብር ስትጠጋ አንዳንዴም ስትዘል ዝምታ፣ የቤት ኪራይ ከመቶዎች ወደ ሺዎች ሲንር ዝምታ፣ የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው ሲያሻቅብ ዝምታ፣ የመብራት፣ የውሃ፣ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በሰአታት፣ ከዚያም ለቀናት አንዳንዴም በተወሰኑ ቦታዎች ለሳምንታት ሲጠፉ ዝምታ፣ መነኮሳት እና አድባራት ሲዘረፉና ሲዋረዱ ዝምታ፣ መስጊዶች እና ኢማሞች ሲዋክቡና ሲታሰሩ ዝምታ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩና ሲሳደዱ ዝምታ፣ የንግዱ ማኅበረሰቡ ሲዋክብና ሲጉላላ ዝምታ፣ ገበሬዎች በማዳበሪያ እዳ ንብረታቸውን ሲነጠቁና ከዛም አልፎ ከትውልድ ትውልድ ያቆዩትን ይዞታቸውን እየተነጠቀ ለውጪ ቱጃሮች ሲቸበቸብ ዝምታ፣ ወንዶች ሚስቶቻቸውና ሴት ልጆቻቸው እፊታቸው ሲደፈሩና ሲጠቁ እያዩ ዝምታ፣ እናቶች ልጆቻቸውና ባሎቻቸው በየወጡበት ሲቀሩ እያዩ ዝምታ፣ በየከተማው የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸ በላያቸው ላይ እንዲፈርስ እየተደረገ ከነልጆቻቸ በየሜዳው ተበትነው ይዞታቸው ለስግብግብ ባለሃብቶች ሲሰጥ ዝምታ፣ የሙያ ማኅበራት ሲጠቁ ዝምታ፣ መምህራኖች ሲዋከቡ ዝምታ፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ‘በድህነት ቅነሳ እስትራቴጂ’ ስም ሲፈናቀሉና ለርሃብ ሲዳረጉ ዝምታ፣ ባለሥልጣናት የከፋ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ሲንቦጫረቁ ዝምታ፣ ሕፃናት ሳይቀሩ በየአደባባዩ ግንባራቸው በጥይት እየተቦደሰ ሲረሸኑ ዝምታ፣ የአገሪቷ የትምህርት ሥርዓት ክፉኛ አቆልቁሎ ትውልድን ወደማክሰም ደረጃ ላይ ሲደርስ እየተመለከትን ዝምታ፣ መንግሥት ድህነትን ሸሽተው ከሃገር የሚሰደዱ ወጣቶችን መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችው እያለና ገንዘብ እየቃረመ ለዘመናዊው ባርነት እያዘጋጀ ፓስፖርት ሰጥቶ ሲያሰድድ ዝምታ፣ በየጎዳናው የወደቁ  ሕፃናቶችን በጉዲፈቻ ስም መንግስት ለውጪ ዜጎች በብዙ ሺ ዶላር ሲቸበችብ እያየን ዝም፣ መንግስት የራሱን ሕገ-መንግስት እየናደ የፈቀደውን ሁሉ በዜጎች ላይ ሲፈጽም የህዝብ ምላሽ ዝምታ፣ ዝምታ፣ ዝምታ…..። ስንቱ ተጠቅሶ ይቻላል?

አንድ ሕዝብ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ያለፋታ ሲዥጎደጎድበት እና መገለጫ የሌልውን ግፍ እና ጭቆና በጫንቃው ላይ ሲጫንበት ውስጥ ውስጡን እያጉረመረመ፣ እያለቀሰና ልቡ እየደማ እንዴት ነህ ሲሉት ደህንነቱን ለመግለጽ ‘እግዚያብሄር/ አላህ ይመስገን’ እያለ የውሸት ሳቅ እየሳቀ እንዲኖር ያስገደደው ምንድን ነው? መንፈሱና አካሉ በቁሙ ተሸርሽረው እያለቁ ባልሞትኩም ባይነት የአያቶቹን ገድል በህሊናው እያመነዥከ በዘመኑ ለተጋረጡበት ፈተናዎች፤ በተለይም ድህነት፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጭቆዎችና በገዛ አገሩ ተዋርዶ መኖርን ለመሸሽ ስደትን ወይም ልመናን ወይም ሕሊናን ቀብሮ ለሥርዓቱ አገልጋይ መሆንን ከማን ተማረ? ይህ ጥልቅ የሆነው ዝምታችን የፍርሃት? ወይስ የትእግስት? ወይስ በፍርሃትና በትእግስተኛነት መካከል ሌላ ደሴት ወይም መንጠልጠያ ስፍራ አለ? እራሳችንን እንጠይቅ!

(ክፍል ሁለት)onetwo

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያሰፈነ ስላለው የፍርሃት ባህል ቀደም ሲል ባሰራጨሁት የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ባለሙያዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለፍርሃት ባህል መስፈን መንሰዔዎች ያሏቸውን ነጥቦች ዘርዝሬ ነበር። በክፍል አንድ ጽሑፌ መግቢያ ላይ እንደገለጽኩት ምንም እንኳን ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫዎች መካከል አንዱ ቢሆንም የዚህ ጽሑፍ ትኩረት በወል የምንጋራቸውና በማኅበረሰብ ደረጃም በሚንጸባረቁት የፍርሃት ምልክቶች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። በመሆኑም በዚህ ክፍል ውስጥ የህሊና እና የአካል ቁስልን ባስከተሉ ትላንቶች ውስጥ ማለፍ የሚፈጥረውን የፍርሃት ቆፈንና የሚያስከትለውን መዘዝ በመቃኘት ፅሑፌን ልደምድም።

በአለማችን ታሪክ ከሰው ልጅ አዕምሮ ተፍቀው የማይወጡና እጅግ አሰቃቂ በመሆናቸው ሲታወሱ የሚኖሩ በርካታ ጦርነቶችና የእርስ በርስ እልቂቶች ተከስተዋል። የመጀመሪያውና የሁለተኛው የአለም ጦርነቶች፣ የኦሽዊትዝ ጭፍጨፋ፣ የአፓርታይድ የግፍ አገዛዝ፣ የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ የተከሰቱትና የሚሊዪኖችን ሕይወት የቀጠፉት እልቂቶች በዋነኝነት ተጠቃሾች ናቸው። እነኚህ በክፉ ክስተትነታቸው በታሪክ የሚወሱት አጋጣሚዎች ካስከተሉት እልቆ መሳፍርት የሌለው ሰብአዊ ቀውስ እና የንብረት ውድመት ባሻገር ከትውልድ ትውልድ የሚወራረስ ትምህርትንም አስተምረው አልፈዋል። በተለይም የምዕራቡ አለም በራሱም ሆነ በርቀት በሌሎች ላይም የተፈጸሙትን እነዚህን መሰል መጥፎ ክስተቶች በአግባቡ በመመርመር፣ መረጃዎችን ሰብስቦና አደራጅቶ በማስቀመጥ፣ በመጽሐፍ ከትቦና እና በፊልም ቀርጾ በማኖር ቀጣዩ ትውልድ እነኚህን መሰል አደጋዎችን ከሚያስከትሉ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ ኃይማኖታዊና ኢኮኖሚያው ቀውሶችና ቅራኔዎች እራሱን በማራቅ ችግሮችን እጅግ በሰለጠነና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ ችለዋል። ዛሬ ላይ ያለው ትውልዳቸውም እነ ናዚ እና ሌሎች አንባገነኖች በታሪካቸው ውስጥ ያደረሱትን ሰቆቃና ግፍ እያሰብ የሚሸማቀቅ ወይም በፍርሃት የሚርድ ሳይሆን ታሪክን በታሪክነቱ ትቶ ሙሉ አቅሙንና ጊዜውን ከሳይንስና ተክኖሎጂ ጋር አዋህዶ በዚህ ምድር ላይ ያሻውን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል።

ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያም ዛሬ ያለችበትን ጂዮግራፊያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌሎች ገጽታዎች ለመላበስ ያበቋት እጅግ በርካታ ክፉ እና በጎ ተበለው የሚጠቀሱ የታሪክ ክስተቶችን አስተናግዳለች። ምንም እንኳን ከላይ ከተጠቀሱት የአለማችን አሰቃቂ ታሪኮች ጋር ባይወዳደርም አገራችንም ከውጭ ወራሪዎች በተሰነዘረባት ጥቃትም ሆነ በልጆቿ መካከል በተከሰቱ የእርስ በእርስ ግጭቶች በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ውድ ልጆቿን አጥታለች። ድህነትን ጠራርጎ ሊያስወግድ ይችል ከነበረው አቅም በላይ በብዙ እጥፍ የሚገመት አንጡራ ሃብቷን በጦርነቶች፣ በግጭቶችና በዘራፊዎች ተነጥቃለች። ይህ እና ሌሎች በርካታ ምክንያቶችም ተደራርበው አገሪቱን ከድሃም ድሃ ተብለው ከሚጠቀሱት አገሮች ተርታ አሰልፈዋታል። እንግዲህ ትልቁ ጥያቄ እኛስ እንደ ሌላው ዓለም ሕዝብ አገራችን ካለፈችበት የረዥም ዘመን ታሪክ እና በየወቅቱ ከተከሰቱ መጥፎና በጎ የታሪክ ክስተቶች ምን ተማርን? ተምረንስ ለዛሬ እኛነታችን ምን አተረፍን? በአያቶቻችን እና በእኛ መካከል በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና በፖለቲካ ተክለ አቋማችንም ሆነ አመለካከታችን ዙሪያ ለውጦች አሉ ወይ? ለውጣችን ቁልቁል ወይስ ካለፉት ወገኖቻችን የህይወት ተመክሮ ትምህርት ወስደን የደረስንበት የላቀ የአስተሳሰብና የኑሮ ደረጃ አለ? የታሪክ መዛግብቶቻችንስ ያለፉ ነገስታቶችን እና የጦር አበጋዞቻቸውን ከማወደስና ገድላቸውን ከመተረክ ባለፈ በቀጣዩ ትውልድ ሕይወት የጎላ ሚና ሊኖራቸ በሚችል መልኩ ተዘጋጅተዋል ወይ? ወይስ ‘እኔ የገሌ ዘር’ እያለ እንዲያዜምና በአያቶቹ ገድል እንዲያቅራራ ብቻ ተደርገው ነው የተዘከሩት? እንደ እኔ እምነት ከምዕራቡ አለም እኛንና ብዙዎች የአፍሪቃ አገራትን ከሚለዩን ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ ከነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሚመነጩ ይመስለኛል።

የዛሬ መቶ እና ሁለት መቶ አመት በፊት የተፈጠሩ የታሪክ ክስተቶችን ፍጹም በተዛባ መልኩ እያጣቀስን ልክ የእኛ የልፋት ውጤት አስመስለን እስኪያልበን የምንፎክርና የምንጨፍር እኛ ነን። ታሪክን እና ጀግኖችን ማወደስ ተገቢ ቢሆንም የኛን ድርሻ እነሱን በማወደስ ብቻ ስንገታው አደጋ ላይ ይጥለናል። እንደ አያቶቻችን ታሪክን መስራት ሲያቅተን ታሪክ ሰሪዎችን በማውሳትና በዜማና በግጥም ማወደስ ብቻ ብንኮፈስ የዛሬውን ማንነታችንን አይሸፍነውም። ይህ በአያቶቻችን ታሪክ ውስጥ ተደብቀን ‘በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ’ እያሉ ማዜም፣ መፎከር፣ ማቅራራትና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ዛሬ ከተጣቡን የድህነት፣ የፖለቲካ ጭቆና እና ማኅበራዊ ቀውስ የማያስጥለን እና ነፃ የማያወጣን እሰከ ሆነ ድረስ ኩራታችን ከድንፋታ አያልፍም። አገሬን እወዳልሁ፣ በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ እያሉ ባንዲራ ለብሶ ማቅራራት በተግባር ካልታገዘ የውሸት ወይም ባዶ ኩራት (false pride) ነው የሚሆነው። እውነተኛ ኩራት የሚመነጨው ከራስ ነው፤ የራስን ማንነትን በማወቅና በመቀበል ላይ የሚመሰረት ነው። ማንነትን አምኖ መቀበል አቅማችንንም አብረን እንድፈትሽ ይረዳል። የዛሬ ባዶነታችንን በአያቶቻችን የታሪክ ገድል እንድንሞላ ወደሚያስገድድ የሞራል ክስረት ውስጥም እንዳንገባ ይረዳናል። የዛሬ ውርደታችንን በአድዋ ድል እና በሌሎች የአያቶቻችን ተጋድሎዎች በተገኙ ስኬቶችን ልንሸፍነው ከመጣር ይልቅ ታሪክ እንድንሰራ ብርታት ይሆነናል።

በሌላ በኩል የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ያሳቀፉንን የዘረኝነት መርዝ እያራባን በታሪክ ተፈጽመዋል የተባሉ አንዳንድ ክስተቶችን እየመነዘርን ‘ያንተ ቅም ቅም አያትህ የእኔን ቅም ቅም አይታቶች በድሎ ነበር፤ ስለዚህ በቅም ቅም አያቶቼ ላይ ያንተ ዘሮች ላደረሱት በደል ኃላፊነቱን አንተ ትወስዳለህ እያልን ድርጊቱን ዛሬ ላይ እንደተፈጠረ በመቁጠር የምንጋጭና ለመነጣጠል እንቅልፍ አጥተን የምናድርም አለን። እራስን እንደተበዳይ ሌላውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ በዳይ በመቁጥርና የተዛባን ታሪክ በመተንተን ለዛሬው በዘረኝነት መርዝ ለተለወሰው የፖለቲካ አጀንዳቸው ማሳኪያነት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካፈር የሚለውሱ ኢትዮጵያዊያኖችም (እነሱ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ቢሉም) ልብ ሊገዙ ይገባል። በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ጎሣዎች በገዛ አገራቸው እኩል መብትና ጥቅም እንዲረጋገጥላቸውና የሁሉም አገር እንድትሆን ከመጣር ይልቅ በዘረኝነት ስሜት ውስጥ ተወጥሮ ኢትዮጵያዊነትን መካድና ከራስ ጎሣ ውጭ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ ጠላት መቁጠር መዘዙ ብዙ ነው። ይህን ለመረዳት ብዙ ምርምር አያስፈልገውም። በቅርባችን ካለችው ከሩዋንዳ ትምህርት መውሰድ ይቻላል። ይህን የዘረኝነት እሳት እየተቀባበሉ የፖለቲካ መታገያቸው ያደረጉ ኃይሎችም ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በስሙ የሚነግዱበት ሕዝብ ሊያወግዛቸው ይገባል።

እርቀን ሳንሄድ የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብንፈትሽ ዛሬ ለምንገኝባቸው እጅግ ውስብስብ እና ፈታኝ ችግሮች መንስዔ የሆኑትን ነገሮች በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን። የችግሮቻችንን ምንጮች እና ያስከተሉብንን መዘዝ በቅጡ መረዳት ከቻልን ከተዘፈቅንበት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ጊዜ ላይወስድብ ይችላል። መወጣጫውም ላይርቀን ይችላል። ትልቁ ጥያቄ ችግሮቻችንን ከመዘርዘር ባለፈ ምንስዔዎቻቸውንም በቅጡ ተረድተነዋል ወይ? እንደ አንድ አገር ሕዝብ በችግሮቻችን እና በችግሮቹ ምንጭ ዙሪያ የጠራ የጋራ ግንዛቤ አለን ወይ? በፖለቲካ እና በሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስንደራጅስ ከነዚህ ግንዛቤዎች ተነስተን ነው ወይ? የጋራ የሆኑ ችግሮች ሰዎችን ያስባስባሉ፣ ለድርጅቶች መፈጠርም መንስዔ ይሆናሉ፣ ችግሮቹንም ለመቋቋም እና ለማስወገድ “ከአንድ ብርቱ …” እንደሚባለው ኃይልን ይፈጥራሉ። ይሁንና ስብስቡ ወይም የተደራጀው ኃይል ፊት ለፊት ከተጋረጡት ችግሮች ጋር ከመፋለም ባለፈ በድጋሚ እንዳይከሰቱ ምንጮቻቸውን ለማድረቅ የሚያስችል እይታ ከሌለው እና አቅሙንም በዚያ ደረጃ ካላሳደገ ይህ አይነቱ ማኅበረሰብ ሁሌም ለተመሳሳይ አደጋዎች የተጋለጥ ነው። የችግሩን መንሰዔ አጥንቶ ምንጩን ለማንጠፍ ከሚያወጣው ጉልበት፣ ገንዘብና ጊዜ የበለጠ አዳዲስ ችግሮች በተከሰቱ ቁጥር ከተኛበት እየባነነ ተነስቶ ችግሮቹን ለመቋቋም የሚያስችሉ ድርጅቶችን ለመፍጠርና ለማፍረስ የሚያወጣው ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት እጅግ የላቀ ነው። በእንዲህ አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ ጠንካራ የሆኑና ልምድ ያካበቱ ድርጅቶችን መፍጠር አይቻልም። ብዙዎቹ ድርጅቶች ሳይጎረምሱ፣ ሳይጎለምሱ እና ሳያረጁ በጨቅላነታቸው ይሞታሉ ወይም ደንዝዘው ስማቸውን ብቻ ይዘው ይቀራሉ። ይህ አይነቱ ማህበረሰብ አውራ የሚሆኑና በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉም የፖለቲካ፣ የኃይማኖት እና የማኅበራዊ ህይወት መሪዎችን የመፍጠር አቅም የለውም፤ አይፈጥርምም፤ በራሳቸው ጥረት ቢፈጠሩም ጎልተው እንዲታዩ እድሉን አይሰጥም። ትላንት ያነገሳቸውን በማግስቱ አፈር ከድሜ ሲደባልቃቸው ምንም አመክንዮ አይፈልግም። ሲያከብርም፣ ሲሾምም፣ ሲያዋርድም ሆነ ሲኮንን በስሜት ነው። በተለይም እንደኛ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ተተብትቦ ግራ ለተጋባ ማኅበረሰብ ልምድና በእውቀት የጎለበቱና የሕዝብ አመኔታን ያገኙ ባለ ዕራይ ድርጅቶችና ግለሰቦች መኖር እጅግ ወሳኝ ነው።

የፖለቲካም ሆነ ሌሎች ልዩነቶቻችንን የምንይዝበት መንገድ ሊፈተሽ ይገባዋል። የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ማብቂያን ተከትሎ የፈረሰውና ጀርመንን ለሁለት ከፍሏት የነበረው ግንብ ሲናድ ምስራቅና ምዕራቡን ወደ አንድ አገር ከመለወጥ ባለፈ መላው አውሮፓን አንድ ያደረገ ክስተትን ፈጥሯል። የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳቦች የልዩነት ማጦዣ ምክንያቶች ከመሆን ወጥተው ጀርመንን ብቻ ሳይሆን አውሮፓን ያዋሃዱ ተጨባጭ እውነታዎችን ፈጥረዋል። ይህን ተከትሎም ከታሪክ ለመማር ዝግጁ በሆኑ በበርካታ የአለማችን አገራት በመሬት የተገነቡም ሆነ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ የተካቡ የልዩነት ግንቦች ሁሉ ፈርሰው ዜጎች ለጋራ ራዕይ በጋራ የመቆም ጽናትን አሳይተዋል። ሕዝባቸውንም ነጻ አውጥተዋል። ሌሎች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ አገሮች (አብላጫዎቹ የአፍሪቃ አገራት) የልዩነቶቻቸውን ግንቦች አጠንክረውና አዳዲስ ግንቦችን በአይምሯቸው ውስጥም ገንብተው የተሰበጣጠረና የሚፈራራ የኅብረተሰብ ክፍልን በመፍጠር ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል። የጎሣ ግንቦች፣ የሥልጣን ግንቦች፣ የኃይማኖት ልዩነት ግንቦች፣ የድሃና የሃብታም ግንቦች፣ የጨቋንና የተጭቋኝ ግንቦች፣ ሌሎች ማኅበረሰቡን በአንድ ላይ እንዳይቆም እና ድህነትና አንባገነንነትን አሽቀንጥሮ እንዳይጥል አቅም የሚያሳጡ በርካታ የልዩነት ግንቦች ተገንብተዋል።

ድርጅቶችን እና መሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን እየፈጠርንና መልሰን እየደፈጠጥን የመጣንበትን የ50 ዓመታት የፖለቲካ ጉዞ ወደ ኋላ መለስ ብለን ብንቃኝ ይህንን እውነታ ያረጋግጥልናል። ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ለቁጥር የሚታክቱ የፖለቲካ፣ የሙያና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ድርጅቶች ተፈጥረው ብዙዎች ካለሙበት ሳይደርሱ ከስመዋል። ጥቂቶችም ባልሞት ባይ ተጋዳይነት በመኖርና ባለመኖር መካከል ሆነው ቀጥለዋል። በከሰሙትም እግር ሌሎች በርካቶች ተተክተው በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ ወድቀው የኅብረተሰቡን ቀልብ ለመሳብ ደፋ ቀና ሲሉ ይስተዋላል። እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው በዚህ ዘመን ውስጥ ብቅ ብለው በከሰሙትም፣ ተውተርትረው ቆይተው በተዳከሙትም፣ አዳዲስ ስም እየያዙ በተፈጠሩትም ድርጅቶች ውስጥ ዋነኛ ተዋናዮቹና የድርጅቶቹ ፈጣሪዎችም ሆኑ አጥፊዎቹ አንድ አይነት ሰዎች መሆናቸው ነው። ትላንት በአንድ ድርጅት ጥላ ስር ሆነው ሌሎችን እንደ ጠላት ይፈርጁ የነበሩ ሰዎች ዛሬ የብዙ ድርጅቶች ፈጣሪዎች ሆነዋል። ትላንት በጠላትነት የሚፈራረጁ ድርጅቶች አባል የነበሩ ሰዎች ቂማቸውን እንዳረገዙ ዛሬ በአንድ ድርጅት ጥላ ሥር የተሰባሰቡበትንም ሁኔታ እናያለን። በድርጅቶቹ መካከል እጅግ ጠባብ የሆኑ የርዕዮታለም ልዩነቶች ከመኖራቸው ውጭ አብዛኛዎቹ የመጨረሻ ግባቸው አንድ እና አንድ ነው። ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ የሕግ ልዕልና የተረጋገጠባት፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት እና ድህነትን ያሸነፈች ኢትዮጵያን ማየት፣ መፍጠር ነው። በነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የሚለያዩ ድርጅቶች ያሉ አይመስለኝም፤ ሊኖርም አይችልም። ልዩነቱ እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ ድርጅቶቹ በሚከተሉት አቅጣጫና መንገድ ቅየሳ ላይ ነው።

በዚህ የ50 ዓመት ጉዞ ውስጥ በሽብር መንፈስና በነውጥ ተግባራት የተሞላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በድርጅቶች መካከል እርስ በርስ አለመተማመንንና መካካድን ፈጥሯል። ይህም አለመግባባቶቹ ከጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት አልፈው እልቂትን አስከትለዋል። በዚያም የተነሳ አገሪቷ በፍርሃት እንድትዋጥና ሕዝቧም በስጋት እንዲኖር፤ የፍርሃት ባህልም እንዲጎለብት ከፍ ያለ ሚና ተጫውቷል። ዛሬ በእያንዳንዳችን አዕምሮ ውስጥ በርካታ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሲቪክ ማኅበራት፣ በኃይማኖት ተቋማት፣ በማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከልም የበርሊን ግንብ አይነት ግዙፍ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። የዛሬዎቹ ኃይሎች ከገዢው ፓርቲ በስተቀር በትጥቅ የተደራጁ ስላልሆኑ ነው እንጂ ለመጠፋፋት ቅርብ ናቸው። ትልቁና እያንዳንዳችን እራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን፤ እነዚህን ግንቦች ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዴት ንደን እና በላያቸው ላይ ተረማምደን ልብ ለልብ እንዋሃዳልን? እንዴት እንደ አንድ ሕዝብ የጋራ ዕራይ፣ የጋራ መዝሙር፣ የጋራ ህልም፣ የጋራ መፈክር፣ የጋራ መድረክና የጋራ አገር እንፈጥራለን? እንዴት ከቂም፣ ከበቀልና ከቁርሾ ሽረን ከታይታና ከቧልት ፖለቲካ ወደ እውነተኛ የፖለቲካ ሕይወት እንመለሳለን?

ለማጠቃለል ያህል በእኔ እምነት ከተተበተብንበት ውስብስብ ችግሮችና ከተጫነን የፍርሃት ድባብ ለመላቀቅ፤ አልፎም ጤናማ የሆነ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሥርዓት ባለቤት የሆነ ማኅበረሰብ ለመፍጠር የሚከተሉት ተግዳሮቶች ቢቀድሙ ይበጃል እላለሁ::

  • ዛሬ ለፖለቲካ ንትርክና  እርስ በርስ መፈራራት እንደ ምክንያት የሚነሱት የታሪካችን ክፍሎች ከፖለቲካ፣ ከኃይማኖት እና ከሌሎች ወገንተኝነት ነጻ በሆኑ ምሁራን በአግባቡ የሚጠኑበት ማዕከል ቢኖረን። የመወዛገቢያ ነጥብ የሆኑትም ታሪካዊ ኩነቶችን በአግባቡ ቢጠኑ እና በተለያዩ መንገዶችም ተደግፈው ለማስተማሪያነት ቢውሉ በድንቁርና ላይ ከተመሰረቱት ታሪክ ጠቀስ የሆኑና በጥላቻ መንፈስ የተሞሉ ክርክሮች ወጥተን እውቀትን በዋጁ ውይይቶች ላይ እናተኩራልን።
  • የሩቁን ለታሪክ ምሁራን እንተወና ባለፉት አምሣ ዓመታት ከ1960 ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ በፖለቲካ ትግል ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑ ኃይሎች ዛሬም በአገሪቷ የለት ተዕለት የፖለቲካ ህይወት ውስጥ በግራና በቀኝ ሆነው እና በመቶ ድርጅቶች ጉያ ውስጥ መሽገው በአገሪቷና በድሃው ሕዝብ እጣፈንታ ላይ ወሳኞች ሆነው ቀጥለዋል። በተለይም ‘ያ ትውልድ’ በሚል የሚታወቀው የኅብረተሰብ ክፍል ከልጅነት እስከ አዋቂነት ክቡር ሕይወቱን፣ ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና እውቀቱን ያለምንም ስስት የዛችን አገር እጣ ፈንታ ለማቅናት መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል፤ ዛሬም ዋነኛ ተዋናይና አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ቀጥሏል። ይህ ትውልድ ትላንትናም ሆነ ዛሬ በገዢና በነጻ አውጪዎቻች ቡድኖች ተፈራርጆ እርስ በርሱ ተጨራርሷል፣ ቂምና ቁርሾም ተጋብቷል፣ ተሰዷል አሰድዷል። ዛሬም በልቡ ቂም ይዞና በቀልን አርግዞ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ መሽጎ የጎሪጥ ይተያያል። ባገኘው አጋጣሚም ሆሉ ይናቆራል። ‘ቂም ተይዞ ጉዞ’ እንዲሉ ትላንት በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው በጠላትነት ይፈራረጁና ሊገዳደሉ ይፍላለጉ የነበሩ ሰዎች ይህን ሸክማቸውን በንስሃ እና በይቅር ባይነት ከላያቸው ላይ ሳያራግፉ ውስጥ ውስጡን እየተብሰከሰኩና እየተፈራሩ ገሚሶቹ በልጅነታቸው በቆረቡባቸው ድርጅቶች እየማሉ ቀሪዎቹም ዘመኑ በወለዳቸው አዳዲስ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው የለበጣ ውህደት እየመሰረቱ በዋዜማው ይፈረካከሳሉ። እንደ እኔ እምነት ከዚህ የእርስ በርስ መፈራረጅ፣ መፈራራትና የቆየ ቂምና ጥላቻ ሳንሽር የምንክበው ካብ ሁሉ የእምቧ ካብ ነው የሚሆነው። እየሆነ ያለውም ይሄው ነው። ከዚህ አዙሪት ወጥተንና ከቂም ተላቀን የጋራ ራዕይ እንዲኖረን እያንዳንዱ ግለሰብ እራሱን ለይቅርታ ማዘጋጀት አለበት። ከልብ የበደላቸውን ይቅርታ ለመጠየቅና ይቅርታ ለመቀበል። ከድርጅታዊ ወገንተኝነትም እራሱን ነጻ አውጥቶ በሱና በድርጅቱ ላይ የተፈጸመውን በደል ብቻ ሳይሆን እሱም ጠላት ብሎ በፈረጃቸው ሰዎችና ድርጅቶች ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ለመናዘዝና ለደረሰውም ሁሉ አቀፍ ጥፋት ድርሻቸውን በድፍረት በማንሳት የተጠታቂነት ባህልን ‘ሀ’ ብለው ሊጀምር ይገባዋል።
  • ይህ ሁኔታም የደረሰውን የጉዳት መጠን በቅጡ እንድናውቅ ከማድረጉም ባሻገር እርስ በርስ የመወነጃጀሉን ታሪክ እንድንገታውና ልባችንንም በፖለቲካ ንስሃ አንጽተን የሚነገርለትን ያህል የተሳካ ባይሆንም እንኳ ልክ እንደ ደቡብ አፍሪቃው ‘በእውነት’ ላይ ወደ ተመሰረተ የእርቅ እና የሰላም መድረክ እንድቀርብ እድል ይፈጥርልናል።
  • የልጆቹን እርስ በርስ መጨራረስ እየተመለከት ፓለቲካ እንዲህ ከሆነ አርፎ መቀመጥ ይበጃል፤ እርም የፖለቲካ ነገር በሚል አይምሮውን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የለት ጉርሱን ብቻ እየቃረመ የአገሩን የፖለቲካ እጣፈንታ ለእዝጌሩ ትቶ ደግ ቀንና መልካም አስተዳደርን እንደመና ከሰማይ እንዲወርድለት የሚጠባበቀውም የኅብረተሰብ ክፍል አይኑን ይገልጣል፤ ከመጠፋፋት ወደ ሰለጠነ የውይይት ባህል በሚሻገረው የፓለቲካ ኃይልም ላይ እምነት ያሳድራል፤ እራሱንም ከፍርሃት ነጻ አውጥቶ በሙሉ ልብ በአገሩ ጉዳይ ባለቤት ይሆናል።
  • ስለዚህም የገዢው ኃይል ወያኔ ካለበት ጥልቅ ፍርሃት እና የሥልጣን ጥም የተነሳ ለእንዲህ ያለው ለውጥም ሆነ የሰላምና የእርቅ ጎዳና ገና ዝግጁ ባይሆንም የተቀሩት የፖለቲካ ሃይሎች መንገዱን በመጀመር ለዘመናት በመካከላቸው የቆየውን ቁርሾና ቂም ከአዕምሯቸው በማውጣት ከልብ የመነጨ እርቅ በማድረግ የልዩነት ግንቦችን ማፈራረስ ይጠበቅባቸውል። የሰላም፣ የእርቅ እና የእውነት አፈላላፉ ጉባዔ ያስፈልገናል።

በእውነት ላይ ተመስርተው ተቃዋሚዎች በቅል ልቦና ከታረቁ አብረው ከሠሩ በኢትዮጵያዊና በኢትዮጵያዊያን ላይ ለዘመናት እንደ መዥገር ተጣብቀው ደማችንን የሚመጡትን፣ ክብራችንን ገፈው እርቃን ያስቀሩንን፤ ድኅነት፣ እርዛት፣ አንባገነናዊ ሥርዓትና ጭቆና፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ጦርነትና የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ድንቁርና፣ ጨለምተኝነት፣ ፍርሃት፣ ሙስና እና ጥላቻን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅለን መጣል እንችላለን። ቅን ልቦና ይኑረን! ለዘመናት የተጫነንን ሸክማችንንም እናራግፍ። ያኔ ለፍቅር በፍቅር፣ ለሰላም በሰላም፣ ለነጻነት በነጻነት፣ ለአንድነታችን በአንድነት የምንሰራበትና ታሪክ ዘካሪ ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪ የምንሆንበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

ቸር እንሰንብት!

ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ

Posted by Hellen Tesfaye

Advertisements

በከፊቾ ዞን የጽላት ዝርፊያና ቀበኞቹ

“ባለሃብቶች በእድሳት ስም ቤተ መቅደስ ዘልቀው ጽላት ይቀይራሉ”

tabot

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በከፊቾ ዞን በጥንታዊ አድባራት ጽላት መዘረፉን እናውቃለን ያሉ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ገለጹ። የዜናው ምንጮች የዞኑ አገረ ስብከት በዞኑ በሚገኙ አድባራት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቀዋል። ዝርፊያውን የሚያካሂዱት “ባለሃብቶች” መቀመጫቸውን አዲስ አበባና ጅማ ከተማ ያደረጉ የክልሉ ተወላጆች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ነዋሪነታቸው ቦንጋና ጊምቦ እንደሆነ የሚገልጹት የዜናው ምንጮች “ቀበኞች” በማለት የሚጠሯቸውን የጽላት ዘራፊዎች የዝርፊያ ስልት ተናግረዋል። በመጀመሪያ እድሜ ጠገብ የሆኑትን አድባራት ይለያሉ። በቃፊሮቻቸው አማካይነት መረባቸውን ዘርግተው ሰዎችን ያጠምዳሉ። ህዝበ ክርስቲያን በሚሰበሰብበት ወቅትና ዓመታዊ የበዓላትን ቀን መርጠው በርዳታና በእድሳት ስም ውዳሴ ይቀበላሉ።

በዞኑ የሚገኙት አቢያተ ክርስቲያናት እድሜ ጠገብ በመሆናቸው በርካታ ጥንታዊ ቅርስም እንዳላቸው የሚጠቁሙት ክፍሎች “ያረጁትን አድባራት እናድሳለን በማለት ጥቁር ለምዳቸውን ለብሰው መቅደስ ውስጥ ይዘልቃሉ” በማለት የዝርፊያው ድራማ እንዴት እንደሚከናወን ያስረዳሉ።

ለሃይማኖታቸው የቀኑና የታመኑ የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችና አገልጋዮች ሲያጋጥሟቸው መቅደስ ውስጥ ተመላልሰው በሚሰበስቡት መረጃ መሰረት አብረቅራቂ ሃሰተኛ ጽላት በመተካት ዝርፊያ እንደሚካሂዱ፣ ለዝርፊያ የሚመችና ስብናው የወደቀ አገልጋይ ሲያገኙም በግልጽ ያሻቸውን አድርገው ስርቆቱን እንደሚፈጽሙ የዜናው ሰዎች ያስረዳሉ።

ድርጊቱ የቆየና ሰዎቹም የሚታወቁ እንደሆኑ የሚጠቁሙት እነዚሁ ክፍሎች፣ “ቀበኞቹ” ካላቸው የገንዘብ አቅም አንጻር እጃቸው ከወቅቱ ጉልበተኞችና የቤተ ክህነት ከፍተኛ አመራሮች ጋርም የጠበቀ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል ከግምት በላይ አመላክተዋል። በዚህ ተነሳ “እንፈራለን፤ ፊት ለፊት ለመግጠምም እንቸገራለን” በማለት ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ምስጢራቸው እንዲጠበቅ አስጠንቅቀው መረጃውን ለመስጠት ችለዋል።

“ይህንን ዜና ጥቅማቸው የሚነካና ችግር ያለባቸው አካላት ዙሪያ ያሉ ጥቅመኞች ሊያስተባብሉት ይችሉ ይሆናል” ሲሉ ዜናው የሚያስደነግጣቸው ክፍሎች የሚወስዱትን የመጀመሪያ ርምጃ ያመላከቱት ተቆርቋሪዎች፣ “የእኛ ጥያቄ ግን ማጣራትና ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ ከታወቀ በኋላ እውነታው እንዲረጋገጥ ነው” ብለዋል።

የዞኑ አገረ ስብከት ዛሬ ነገ ሳይል በተቀደሱ የማምለኪያ አድባራት ላይ የተፈጸመውንና እየተፈጸመ ያለውን ዝርፊያ የማጣራት ሃላፊነት እንዳለበት ያሳሰቡት ክፍሎች፣ ቀበኞቹ በርዳታ ስም እድሳት ባካሄዱባቸው አድባራት ላይ የሙከራ ምርመራ ቢደረግ ጥቆማው ምላሽ እንደሚያገኝም በርግጠኛነት ተናግረዋል።

በእድሳትና በርዳታ ስም መቅደስ በመዝለቅ ከሚከናወነው ዝርፊያ በተለየ በድርድር የሚካሄዱም ዝርፊያዎች ስለመኖራቸው ያመለከቱት ክፍሎች “ጉዳዩ እጅግ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ስምና ቦታን ለይተን ለመጠቆም እንቸገራለን” ብለዋል። “መልዕክቱ ለቀበኞቹ፣ ለተባባሪዎቻቸውና የሚሰማ ተቆጣጣሪ አካል ካለ ለነሱ ነው” ሲሉም አክለዋል። በዞኑ ያሉ የህዝብ ወኪል እንደራሴዎችም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥንቃቄ ወስደው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

“የቃል ኪዳን ጽላት ዘርፎ ከማነከስና ሰልሎ ከመሞት ውጪ ሌላ ዕድል የለም” ሲሉ ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉት ተቆርቋሪ አዛውንቶች በ2005 መገባደጃ ላይ ዋሻ ውስጥ ተገኘ የተባለ ጽላት የት እንደገባ እንደማይታወቅ አመልክተዋል። ዜናው የመገናኛ ሰዎች ዘንድ ሁሉ ደርሶ እንደነበር፣ ነገር ግን በማይታወቅ ሁኔታ ተዳፍኖ መቅረቱ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አካላትን እስካሁን እንደሚከነክናቸው አመልክተዋል።

ከዝግጅት ክፍሉ

ይህ ዜና ከመታተሙ በፊት ከጥቆማው በተጨማሪ ሰዎችን ለማነጋገር ተሞክሯል። የዞኑን አገረ ስብከት ለማግኘትም ተሞክሯል። ከዜናው ባህሪ በመነሳት ጉዳዩ ሳይጣራ ግለሰቦችን የሚያመላክቱ መገለጫዎችን ከመጠቀም ተቆጥበናል። በተጠቀሰው ቦታ ብቻ ሳይሆን በመላው አገሪቱ በርካታ ቦታዎች ነዋያትና ጥንታዊ ቅርሶች እንደሚዘረፉና ለዝርፊያው ተባባሪ ሆነው የሚያገለግሉት የድንበር ጠባቂዎች መሆናቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚሰማ እውነት በመሆኑ ተጨማሪ ጥቆማ ለምታቀርቡልን መድረኩ ክፍት ነው። ከቦንጋና አካባቢው፣ እንዲሁም ከጅማ ነዋሪዎች ለደረሰን ጥቆማ እናመሰግናለን። በዜናው ላይ ቅሬታም ሆነ ተቃውሞ ካለ እናስተናግዳለን።

goolgule.com

Posted by Hellen Tesfaye

ኔልሰን ማንዴላ በሕይወት ቢለዩንም በመንፈስ አብረውን ይቆያሉ

 

በአፓርታይድ የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ብቻ ሳይሆን በዩ. ኤስ. አሜሪካ ጭምር ሽብርተኛ ተብለው ሲሳደዱ፣ ሲታሰሩና ሲሰቃዩ የሕይወታቸውን አጋማሽ የጨረሱ፤ በመሣሪያ የታገዘ አመጽንና ሕዝባዊ እምቢተኝነትን አጣምሮ የያዘ ሁለ-ገብ ትግል በመምራት ለአፓርታይድ አገዛዝ ማብቃት ከፍተኛ ድርሻ ያለው የትግል አስተዋጽዖ ያደረጉ፤ ለመላው ዓለም የነፃነት ታጋዮች አርአያ የሆኑት ኔልሰን ማንዴላ አረፉ።

ኔልሰን ማንዴላ የነፃነት ትግልን በግንባር በመሰለፍ መርተዋል። ኢትዮጵያ ድረስ በመምጣት ወታደራዊ ሥልጠና ወስደው ዘረኛዉን የፕሪቶሪያ አገዛዝ በመሣሪያ ታግለዋል። የእሳቸው ጠመንጃ ማንሳት ለበርካታ ወጣት ታጋዮች አርዓያ ሆኗል። እስር ቤት በቆዩባቸው 27 ዓመታት ደግሞ የድርጅታቸውንና የትግሉን አመራሩ ለጓዶቻቸው በመተው እርሳቸው ለነፃነትና ለእኩልነት በመታሰርና ስቃይን በመቀበል ትግሉን መርተዋል። በዚህም ምክንያት በትግል ሜዳም በእስር ቤትም መሪ እንደሆኑ የዘለቁ ታላቅ አፍሪቃዊ ናቸው።

ከነፃነት በኋላ ደግሞ ኔልሰን ማንዴላ በሕዝብ ነፃ ፈቃድ የተመረጡ የአዲሲቷ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንትነት ሆነዋል። በየምርጫው ተወዳድሬ አሸንፌ በፕሬዚዳንትነት ልቀጥል ሳይሉ በአፍሪቃ ባልተለመደ ሁኔታም አንድ ዙር ብቻ አገልግለው ደግመው ላለመወዳደር ወስነው በጊዜ ሥልጣናቸውን በመልቀቅ መርተዋል። በመሆኑም ኔልሰን ማንዴላ ሥልጣን ላይ ሆነውም ሥልጣን ለቅቀውም መሪ መሆን የቻሉ ድንቅ አፍሪቃዊ ናቸው።

ኔልሰን ማንዴላ ታላቅ የነፃነት አርበኛ፣ ታላቅ የለውጥ አራማጅ፣ ታላቅ መምህር እና ታላቅ የእርቅ ሰው ነበሩ። ዛሬ ዓለም እኚህን ታላቅ አፍሪቃዊ አጣች።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በኔልሰን ማንዴላ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል። ከእንግዲህ ማንዴላን የምናስባቸው ከእሳቸው ተሞክሮ የምንማረው ሲኖር ነው። በዘረኝነት እየተጠቃን ላለነው ኢትዮጵያዊያን የማንዴላ ትምህርት ሕያው ሊሆን ይገባል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ዘረኝነትን በጽናት የመታገል ሆኖም ግን ይቅር ባይ የመሆንን እሴቶች ተግባራዊ በማድረግ ማንዴላ በሕይወት ቢለዩንም በመንፈስ ሁሌም አብረውን እንዲኖሩ እናድርግ ይላል።

የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህዝብ ግንኙነት

Posted by Hellen Tesfaye

አዲሱ ነጠላ ዜማ፣ ድርድር

– ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

በሳውዲ የተነሳው የወገን ሰቆቃ ገና አልበረደም። ስቃዩ የበለጠ ሲከፋ እንጂ ሲቀንስ አላየንም። ለውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲባል ልክ እንደ ባርያ ንግድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል የተላኩት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በገዥው ፓርቲ እንደታሰበው አልሆነም። እንዲያውም ሌሎች መዘዞችን አስከትሎ መጥቷል። ዲያስፖራው እንደገና ተነሳ። ለቦንድ ግዢና ለግንቦት ሃያ በዓላት የሚሰባሰቡትም ጭምር ገዢው ፓርቲን ማውገዝ ጀመሩ። የስደተኛው ጎርፍም እንደሱናሚ ማእበል ያንን ጎራ ማጨናነቁ ግልጽ ነው። ወቅት እየጠበቀ የሚነሳው የክረምቱ ነቀርሳ አሁን በነበረከት ስምዖን ላይ ጠና ያለ ይመስላል። ይህ ህመም ማስታገሻ ያስፈልገዋል። ዘላቂ ሳይሆን ግዚያዊ ማስታገሻ። መቼም ለነቀርሳ ዘላቂ መፍትሄ የለውም። ለግዜው ግን እድሜ ማራዘሚያ … የድርድር ጥያቄ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

ADDIS STANDARD’S EXCLUSIVE INTERVIEW WITH ANA GOMES

 

Ana Gomez
Ana Gomes is coordinator and spokesperson of the foreign affairs committee for her political group, the Social-Democrat. With 200 members the Social-Democrat is the second largest group within the European Parliament. For Ethiopia and Ethiopians though Ana Gomes is best remembered for her role as the leader of the EU election observers’ team during the 2005 crisis-induced general election in Ethiopia. She has had a troubled relationship with Ethiopia’s late Prime Minister Meles Zenawi, who she still calls “a dictator,” after she published her report in which wrote the election was massively rigged. Eight years later, Ana Gomes came to Ethiopia to participate in the just concluded 26th ACP-EU parliamentary meeting. Her arrival in Addis Ababa caught many, who thought she would never be allowed to set foot in Ethiopia, by a surprise. Addis Standard’s deputy-editor-in-chief Tesfaye Ejigu met Ana Gomes during the meeting and held an exclusive interview. Excerpts:  

AS – Your question to the development commissioner Andris Piebalgs was on Ethio-Djibouti road project funded by the EU. The commissioner replied EU no longer funds road projects in Ethiopia because construction work is given to companies without auction or given to friendly companies. What happened to the Ethio-Djibouti road project at the end?

Ana- Gomes – I don’t know if it was the auction. I raised the issue because some very concerned European friends told me about that because there is a lot of money from the European taxpayers which was supposed to be directed to development that was diverted. I only talked about the road. But I just confirmed with the EU commission representative that it’s indeed two contracts; one, a railway between Addis Ababa and Djibouti; the EU funding was around 45 million Euros, and two, 50 water tunnels project, by the same company worth 20 million Euros. The company was an Italian company called CONSTAT. That company adds Ethiopian Contractors/subcontractors. Obviously it was chosen by the ministry of finance with EU agreement. It’s a project that has gone very wrong because nothing has been achieved, and the money has been deviated.  EU has started investigation, arbitration is going on; it also involved your government.  And support has been cancelled. They are apparently trying to recover the money from the company. But the money has gone, so the investigation goes on. I was promised for the details by the European commission. It doesn’t mention road. It’s a bit weird however that the EU development commissioner mentioned road construction. And the EU signing new agreement to fund road projects in Ethiopia is contradictory. I think it’s important to clarify all these contradictions for the sake of taxpayers in Europe and also for the Ethiopian people. I am heartened by the fact that PM Hailemariam [Desalegn] has started taking measures even against the high officials who are involved in corruption. So I have to find out. In fighting corruption the main element is transparency. So this element has to be put out for the people to know. There are some things to be checked.qoute2

 AS – EU funded hydropower project-Gilgel gibe 3 was given without auction to Salini Construction, an Italian company. A few months after it went operational part of it caved in and was closed. The EU criticized openly the handing out of the construction without auction. But it didn’t decide not to fund hydropower projects.

 Ana Gomes – I am very interested to learn about that. I need to note down that information. I will find out about it and ask the EU.  I am glad you asked this. I have not been able to follow in detail all this development processes because I was not in the EU development committee.

 AS – ACP-EU joint parliamentary assembly has democratic agenda. The speaker of the house of people’s representative of Ethiopia Abadula Gemeda said, “we have achieved a lot in building democracy, peace and good governance.” Do you buy that? Do you think a lot has been achieve?  

 Ana Gomes – No! In many respect I see a lot of the old ways. Meles was an expert in using jargons such as good governance, the rule of law, democracy, sustainable development, but in practice doing just the opposite. It was a smart leadership which uses politically correct languages for Europeans and Americans consumption. But the practice was really oppressive. What I saw during Meles Zenawi was a dictatorship. I have lived in dictatorship in my own country. I believe this persists in the mind set of many authorities.

But at the same time, I realize there is indeed some opening, some realization [that] Ethiopia can’t continue this way.  Ethiopia needs change. Even some of the people who have that politically correct speech that everything has been achieved in Ethiopia in public, in private conversation with me they acknowledged that Ethiopia needs change, and that it is the time to really promote important, drastic changes. In that sense I welcome the move that the PM Hailemariam has initiated the prosecution of high officials, even a minister charged with corruption. I hope this will be the first step in the right direction. At the debate we were discussing the independence of the judiciary.  I used the debate to say that Judicial Independence doesn’t exist in Ethiopia, although it’s stated. I recalled the judges who flee the country in 2005 because they refuse to tamper with the conclusion on the inquiry about the massacre in 2005. They were pressed by the [late] PM and the government to do that. These were very courageous people who put all their lives and their families [at risk].  I also highlighted that trials of all political prisoners but in particular journalists Eskinder Nega, Wubeshet Taye, Riyot Alemu and others like DebebeEshetu; [political] leaders Andualem Arage e.t.c. were not fair; all the people [including] Europeans who were able to be present at some of these trials said they [the prosecutors] never produced any significant evidence against them and indeed the trials were not fair.  So I hope I have made this appeal today here.

 AS – But they faced terrorism charges…?

These terrorist charges are not credible, so I appeal for their liberation in the spirit of openness. You have now a sort of dual register. In public it said one thing in private it acknowledges that Ethiopia must change. Or Ethiopia needs support to change. In that context, indeed bold decisions should be taken to liberate these people, because some of these people are icons of the younger generation. Very educated, qualified generation which Ethiopia needs to develop itself. I receive a mail, a standard letter everyday from an Ethiopian who manages to flee the country and who is somewhere in Kenya, Uganda ….Nigeria asking me to write a letter to the UNHCR saying they need political asylum. So I know Ethiopia looses the best, most qualified generation not only because of lack of jobs but because there is politically closed environment with which these young qualified people cannot live. I know Ethiopia faces serious terrorist threat as we all do, Ethiopia in particular because of the neighborhood and the tension that has been built up by Meles Zenawi between Muslims and Christians inside Ethiopia which was not an issue in 2005 but in the meantime became a big source of concern.  If the government continues the old ways repressing this bright, younger people who are now connected to the world in a way the regime cannot control them via the twitter, and facebook, and so on. Obviously many of these young people will be driven into the hands of radicals and extremists. Even to be recruited by terrorists.  It is what we see happening in other countries in the region. So, it is very important to open up democratically for the security of the country.

 AS – in 2015 Ethiopia will hold a general election. Do you think it will be democratic, free and fair given the situation now?

qoute1 Ana Gomes – I don’t know, but I hope it could be good. Meles died, he was the source of the repression;his own supporting group are divided. They are fighting with each other. There is indeed an opportunity to see Ethiopia change progressively, peacefully. Nobody wants to see Ethiopia destabilized. But to create the conditions for the election to be held democratically it requires the opposition to be allowed to operate, which is not the case in the moment. In the moment you have only one member of the opposition [in the parliament]. I recall in 2005 at least there were some results that were not disputed. And these are the results of Addis Ababa where all the 23 seats went in a shocking landslide victory to the opposition. Well, where are these people? In exile.

They say the opposition is weak, of course it is weak. “it is weak, it is fragmented, it is not loyal…” are the same kind of things that I used to hear in 2005 from Meles Zenawi. But any opposition in that condition in any country would be weak. In my own country do you think the opposition in the days of the dictator was stronger? No!  Most of it was underground. In order to have the conditions to operate I believe it is important to allow the opposition to operate, not just those inside the country but also those forced into exile. They need guarantee to operate. There is no media freedom, only an opening seen. I read the Ethiopian herald and it’s all the same thing only better because PM Meles Zenawi is not writing now. There is no condition for NGOs or civil societies to operate. I believe EU will not accept to come back and observe election and give its temp of credibility unless basic elements are met; such as liberating political prisoners or allowing the judiciary to operate independently.

 AS – “Europe could definitely make the difference for democracy in Ethiopia. Instead, current European leaders are choosing to fail it. In doing so they are not just failing Ethiopians. They are also failing Europe.” This is taken from a letter you wrote to AP. By this do you mean Europeans aren’t trustworthy? They don’t like democracy to thrive in Ethiopia?

 Ana Gomes – No! European citizens, European taxpayers, European Parliamentarians  care about Ethiopia, democracy, development in  Ethiopia, the efficiency of development assistance but the problem is they don’t know what happens in Ethiopia. They are fooled by the leaders; leaders in the council of ministers and in the European commission. And also the development industry prevailing should continue without trouble. That is their vested interest. The tragedy is many people don’t understand what is happening in Ethiopia.  I was very happy that finally EU human rights sub-committee came last July. They are very serious, knowledgeable colleagues of mine. It was eye opener. They asked to visit Kalite Prison and the PM allowed them but was rudely treated by the Prison administration. That is an eye opener.

 AS – EU and Ethiopia are development partners today as well as then. When you were not on good terms with the regime in 2005 did EU stand by your side?

 Ana Gomes – The then commissioner in charge of foreign affairs and human rights stood by me always. She was not from my party but very serious. I appreciated. But the then development commissioner Mr. Louis Michel didn’t support me. Some people from his services in Brussels even tried to rewrite my report to water it down. I didn’t accept that. Several moments, my views were attacked. They supported the campaign against me which the government of MelesZ enawi spread. But Meles has gone! This is a new timing. I am pleased I was granted visa without preconditions.

  AS – You were lobbying with the EU member states accusing the Ethiopian government of violating human rights. Do you think the situation has improved now?

 Ana Gomes – I know it was not easy for the new PM to assert his role as PM.  I know there was a lot of internal fighting within the power. He is not a Tigrian.  I value the visa I was given. I value the move against corruption. I sense some change.

 AS – I saw you with the speaker of the house of people’s representative, AbadulaGemeda and Ambassador Teshome Toga. You had lunch with them may be. But you were not on good terms with them?

 Ana Gomes – There was nothing personal; even with Meles Zenawi.  Even these professionals who were instrumental, I have nothing personal against them.  I don’t pretend to know well this country.  Ethiopian people really marveled me. Ethiopia has a great resonance in my country.  My ancestors 500 years ago were looking for Prester John.  However, Ethiopia has a magical resonance in my childhood. Ethiopia is special. Ethiopia is a civilization; not any country. It is a civilization.

Anna Gomez AS – You said “the EU is not only misusing European taxpayer’s money, but supporting an illegitimate status-quo, letting down all those who fight for justice and democracy and increasing the potential for conflict in Ethiopia and Africa.” But conflict in Ethiopia rises sometimes due to terrorist threats. Do you agree?

 Ana Gomes – Not only the Muslim-Christian conflict Meles Zenawi fueled by trying to interfere in the Muslim community leadership but also in Ogaden.  All the report we receive in the EU are disastrous, horrendous and I am very sorry to see the Ethiopian army involved in all of thatTerrorism is an excuse; subversion was in the days of the dictatorship in my country.  Now the buzzword is terrorism. It serves to excuse, and to erase any rules, principles and values. I don’t accept it. I am very conscience of the terrorist threat. It is strong democratic societies who are better empowered to fight terrorism, not those with high level of poverty, unemployment and of internal conflict. That is the situation in Ethiopia now. I hope this can be sorted out.

AS – “Western leaders resist speaking up against Zenawi’s regime by invoking stability interests. Besides attempting to depict Ethiopia as a success story of development assistance, EU and the US like to portray their ‘aid darling’ as a partner in the fight against terrorism and a crucial actor for stability in the horn Africa,” do you still believe in this statement of yours?

 Ana Gomes – I hope Ethiopian people will be able to make the distinction between this bankrupt leadership in Europe which brought us into the big economic crises which is also political crises and the people of Europe who really are serious about democracy, human rights and the rule of law.

 AS – Do you think the EU and the USA still see the regime as a partner and a crucial actor for stability or do you see any change in their position?

Ana Gomes –  I think they do. But on the other hand they also appreciate the limits of that partnership in the sense that they understand the big tensions that have been developing in Ethiopia and in the region; namely lack of effectiveness in fighting terrorism and deterring terrorism to infiltrate. I think the Americans understand it better.

Within the Obama administration there is a realization that you cannot have security without real development, not fake development and numbers but without democracy. The Americans were much more effective in getting people out of jail. The American’s pressure had political prisoners freed; opposition leaders and Birtukan Medeksa and others. They realized these three elements are linked, although they have their own flout in fighting terrorism. I was told the new American ambassador to Ethiopia is outspoken about human rights. I hope it translates into a more principled approach on the part of the Obama administration.

 AS – a lot of Ethiopians respect you. They gave you an Ethiopian name. Ethiopians like honesty. Are you aware of your name? Do you know what it means?

 Ana Gomes – Yes! I am aware of it. Ethiopian friends told me about it. They told me “Ana Gobeze” I am flattered, I don’t deserve it. They told me that ‘Gobez’ means brave. I have been happy meeting Ethiopian community in different countries and also received fantastic ‘Kaba’ as a gift from Ethiopians inSweden.

በሳውድ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደቀጠለ ነው

 

 ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት ስትርሀ እየተባሉ በሚጠሩ የማጎሪያ ካምፖች ውስጥ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ።

በውሀ እና በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ እርጉዝ ሴቶች፣ ህጻናትና እናቶች አሁንም የድረሱልን ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊን ምግብ እና ውሀ ለመግዛት ወጣ ሲሉ እንደሚገደሉ ጓደኞቻቸው የተገደሉባቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል

የኢሳት የአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደገለጸው ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት በአይ ኦ ኤም ወጪ ህክምና እየተሰጣቸው ሲሆን ብዙዎች ከአካል ጉዳት በተጨማሪ ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመውን ግፍ ለመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል። በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ረቡእ እለት በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የሳውዲን ንጉስ ፎቶ ግራፍ አቃጥለዋል። ሀሙስ እለት ደግሞ በስፔን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማድሪድ በሚገኘው የሳወዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ኢትዮጵያውያኑ አቤቱታቸውን ለሳውዲ ኢምባሲ ተወካይ ማቅረባቸውም ታውቋል;፡

Posted by Hellen Tesfaye

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

 

Ginbot 7 weekly editorialበሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።

ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።

እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus, the Minister of Foreign Affairs of Ethiopia.

እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።

በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።

የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።

ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።

ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።

እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።

ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ginbot7.org

Posted by Hellen Tesfaye

ብሄራዊ ውርደት፤ የምንመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’

ክንፉ አሰፋ 

ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል[1]። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።

ሰው ከሞተ በኋላ ለምን ሙት አካሉን ማሰቃየት አስፈለገ? ምን አይነት ጭካኔ ነው? ምን አይነትስ ጥላቻ ነው? ለሳውዲዎች ግማሽ ፈረንሳይን የሚያህል መሬት ሰጥተናቸው የለም እንዴ? ሀጥያታችን ምኑ ላይ ነው ታዲያ? አስከሬኑን ውሻ፣ ውሻ ሲሉ ሲሳለቁበት ከማየት በላይ የሚያም ነገር የለም።  በአደባባይ እንደዋዛ የተጣለው አስከሬን በእርግጥ የዉሻ አስከሬን ቢሆን ኖሮ የእንስሳ ተከራካሪዎች  አለምን ቀውጢ ባደረጓት ነበር።

መገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊ ድረ-ገጾች ይህንን ጉዳይ በስፋት ቢዘግቡትም፤ አለም አቀፉ ህብረተሰብ ግን ዝምታን መርጧል። በዚህ በሰለጠነ ዘመን፤ እንደ እንስሳ እየታደኑ ከሚያዙትና ከሚገደሉት ወገኖች ውስጥ አንድ አሜሪካዊ ዜጋ ቢገኝበት ኖሮ ትርምሱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚደርስ እናይ ነበር። የኛስ ነብስ የሰብአዊ ፍጡር ነብስ አይደለችም እንዴ? ስንቀጠቀጥ፣ ስንታረድና ስንገደል የሚፈሰን ደም ከሌላው ዜጋ የተለየ ደም ነው? ግፉ ለምን በኛ ላይ ብቻ በረታ? ሌላ ዜጋ ሲገደል አላየን። እየተሳደዱ የሚታጎሩት ሁሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ይህ ሁሉ ግፍ እና መከራ ለምን በኢትዮጵያዊያን ላይ ብቻ? ድህነታች የዜግነት ክብራችንን አስነጥቆን ይሆን? እርግጥ ነው። የገንዘብ ድሆች ልንሆን እንችላለን። የአስተሳሰብና የስነ-ምግባር ድሆች ግን አይደለንም።

ችግሩ ያለው ሌላ ቦታ ነው። ብሄራውነት የሚሰማው መንግስት፤ ብሄራዊ ክብራችንንና ማንነታች የሚያስመልስ። በአለም አቀፍ መድረክ የሚያስከብረን ጠንካራ አካል ማጣታችን ነው የውርደታችን ምክንያቱ።

እንግዲህ ይህ ነው አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት ቅርስ እና ውርስ። ይኸው ነው ገዢው ፓርቲ የሚመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’። በምእራብ አፍሪካ ኮሌጆች የኢትዮጵያ ታሪክ እንደኮርስ ይሰጣል። የአድዋ ገድል፣ የጸረ-ቅኝ ግዛት ተምሳሌት፣ የነ ማርክስ ጋርቤይ፣ የነ ክዋሜ ንክሩማ፣ የነ ጆሞ ኬንያታ ለነጻነት ትግል መነሳሳት ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ተቆራኝቶ በታሪክ ይዘከራል። ላለፉት 20 አመታት የተፈጠረው ክስተት ግን ይህንን ሁሉ መልካም ስም ድራሹን እያጠፋው ይገኛል። የተስፋይቱ ምድር እያሉ የሚጠሩዋት ራስ ተፈሪያን  የዛሬዩቱን ኢትዮጵያ የውርደት ታሪክ  እንዴት እንደሚያዩት እንጃ። ለአፍሪካ ነጻነት ተምሳሌት የሆንን ሰዎች ዛሬ ስደትን እንደመፍትሄ ለመውሰድ ተገደድን። በስደቱ ብቻ ሳያበቃ ሰብአዊነት በማይሰማቸው አካላት እነሆ ብሄራዊ ውርደትን እየተከናነብነው እንገኛለን።

እ.ኤ.አ. በ2004 የደች ንግስት ቢያትሪክስ ታይላንድ ተጉዛ ነበር። ቢያትሪክስ ወደ ታይላንድ የተጓዘችበት ዋነኛው ምክንያት በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ታስረው የነበሩ ሁለት ሆላንዳውያንን ለማስፈታት ነው። አርባ እና ሃምሳ አመት ተፈርሮባቸው የነበረው እነዚህ ዜጎች በንግስቲቱ ጉብኝት ወቅት እንዲፈቱ ተደረገ።  የታይላንድና የሆላንድ የኢኮኖሚ ግንኙነት በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አረቢያ ካለው የንግድ ትስስር በልጦ አይደለም። ንግስቲቱ በባዶ እጅዋ ወንጀለኛ ዜጎችዋን ማስፈታት ቻለች። ለዜጎችዋ ክብር ስለነበራት። በርግጥ ወንጀል ሰርተዋል። ቅጣቱን እኛው እንስጣቸው ብላ ዜጎችዋን ይዛ ተመለሰች ንግስት ቢያትሪክስ። ሳውዲ አረቢያ የኔዘርላንድን ቆዳ ስፋት በእጥፍ የሚበልጥ መሬት ከኢትዮጵያ ተችራለች። በወንጀል ሳይሆን ይልቁንም በጉልበት ስራ የተሰማሩ ዜጎቻችን የሚፈጸምባቸውን ግፍ ለማስቆም አንድ ሄክታር መሬት ብቻ በቂ ነበር። ሳውዲ በኢትዮጵያ ከ200,000 በላይ ሄክታር ለም መሬት ይዛለች።  ለብሄራው ውድቀታችን እና ውርደታችን ዋነኛው ምክንያት የዜጎቹን ክብር የሚያስቀድም ብሄራዊ  መንግስት ስላጣን እንጂ በዚህ ብቻ ሳውዲን ማስፈራራት ይቻል ነበር።

በሳውዲ ያለው ኢትዮጵያዊ ከ30 ሺህ በላይ ይገመታል። በጉልበቱ ጥሮ እያደረ ያለን ዜጋ ህገወጥ እያሉ ያሳድዱታል። እነሱ ግን በሃገራችን ላይ  እንደአንደኛ ዜጋ በነጻነት የመኖር መብት ተሰጥቷቸዋል። ለሳውዲ ባለሃብቶች የተሰጠው ለም መሬት ለነዚህ ዜጎች ቢሰጥ ኖሮ፤ ወገኖቻችን ባልተሰደዱና ባልተዋረዱ ነበር። 

የኛ ትውልድ፤ ሀገር አልባ፣ ዜግነት አልባ ትውልድ። ከዚህ በላይ የሆነ ብሄራዊ ውርደት የለም።

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ በላከው ማስታወሻ እንዲህ ይላል፤…

…የእኛን መያዝ የተመለከቱ የሳውዲ ወጣቶች (ሸባቦች) ሚስት እህቶቻችን ይደፍራሉ፣ ንብረታችን ይዘርፋሉ!  ይህ ለሶስት ቀናት ሲቀጥል የደረሰልን የለም! ኢንባሲ ደወልን ምንም ማድረግ አንችልም ይሉናል፣ አንተም ድምጻችንን ታሰማናለህ ብለን ብንደውልልህ ፈራህ መሰል አታነሳልንም! የት እንድረስ? ምን እናድርግ?  ንብረታችን እየተዘረፍን ሴቶቻችን  እየተደፈሩ ዝም ብለን ማየት ነበረብን?  ይህን በመቃወም ሻንጣና ቤተሰቦቻችንን  ይዘን ወደ ሃገራችን ስደዱን ነው ያልናቸው“  የሚል እየተቆጣና ድምጹን ከፍ እያደረገ መልስ የሰጠኝን አንድ ወንድም መጨረሻችሁ ምን ሊሆን ይችላል ? አልኩት “… ወደ ሃገራችን ከነሚስት እህቶቻችን ይውሰዱን ነው የምንለው! ያለበለዚያ መንፉሃን እና ሚስት እህቶቻችን አንለቅም! ገድለው ያስለቅቁን” ሲል ክችም ያለ መልሱን ሰጥቶ ስልኩን ጀሮየ ላይ ዘጋው…

በርግጥ ድርጊቱ አዲስ አይደለም። በአረብ ሃገር ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሌም ይታደናሉ፣ ይደበደባሉ፤  ይገደላሉ፤  እህቶቻችን በግፍ ይደፈራሉ። በባርነት ዘመን እንደሰማነው ሁሉ፤ አሳዳሪዎቻቸው እንደ እቃ ይዋዋሱዋቸዋል። ሲከፋቸ ደግሞ የፈላ ውሃ በቁማቸው ይደፉባቸዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን አቤት የሚልላቸው፤ መብታቸውን የሚያስከብርላቸው መንግስት የለም። ሸዋዬ ሞላን የጋዳፊ ቤተሰቦች በቁምዋ ሲይቃጥሏት ይጮህ የነበረው ዲያስፖራው ነበር። ጋዳፊን የነቀለው የሊቢያ አብዮት ሲፋፋም፤ በሊቢያ ነዋሪ የነበሩ የውጭ ዜጎች በየኤምባሲያቸው ሲጠለሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን መግቢያ አጥተው ነበር። የኋላ ኋላ በሱዳንና በናይጄርያ ኤምባሲዎች እንዲጠለሉ ተደረገ። በግብጽና በሶሪያም ተመሳሳይ ክስተቶች ተፈጽሟል። በዱባይና በሊባነን በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ሴት እህቶቻችን ላይ ያላግባብ የሞት ፍርድ ሲፈረድ፤ ይከራከሩ የነበሩት ኢትዮጵያውያን የሲቪክ ማህበራት ናቸው። የዜጋውን መብት የሚያስቀድም ብሄራዊ መንግስት ቢኖረን ኖሮ እንዲህ ባልተደፈርን ነበር።

አንድ የዚህ ሰለባ የሆነ ወገናችን በፌስቡክ ገጽ ላይ እንዲህ ብሎ ጽፏል።

መንግስታችንኢትዮዽያውያን አርሶአደሮችና ነባር ነዋሪዎችን ከቀያቸው እየነቀለና እያፈናቀለ ለም መሬታችን ለሳዑዲ ባለሃብቶች በመናኛ ዋጋ ይቸበችባል። መሬታቸውን በወያኔ የተነጠቁ ወጣቶቻችን ስራ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ ይሰደዳሉ። በአፀፋው ዐረቦች የተሰደዱ ኢትዮዽያውያን ይገድላሉ። የሳዑዲ ባለሃብቶች ግን መሬታችን ይዘው በገዛ ሀገራችን እንደፈለጉ ይፈነጫሉ። የኢትዮዽያመንግስት በችግር ላይ ካሉ የኛ ዜጎች ይልቅ ለሳዑዲ ባለሃብቶች ደህንነት የሚጨነቅ ይመስላል። በእውነት እንደው መቼ ነው ለኛ ደህንነት የሚቆረቆር መንግስት የሚኖረን?

እርግጥ ነው። መንግስታችን ለዜጋው ግድ አይሰጠውም። ሲጀመር ዜጋው ከሀገሩ እንዲሰደድ ያደረገው ብልሹ የሆነ ስርአቱ ነው። እርግማን ይመስል ወገናችን በገዛ ሀገሩ የሚደርስበት በደል በስደት ከሚደርስበት ግፍ አይተናነስም። እዚህም ስቃይ እዚያም ስቃይ። የዘመኑ ወጣት በሁለት ጎን በተሳለ ሰይፍ ገፈት ቀማሽ…።

The suffering of Ethiopians in Saudi Arabia

የሃይሌ ገሪማን  ’ጤዛ’ ፊልም ያስተውሏል? አንበርበር ከጀርመን ሃገር ክብሩን እና አንድ እግሩን ይዞ እትብቱ ወደተቀበረባት ቀዬ ተመለሰ።  አንድ እግሩን በኒዮ-ናዚዎች አጣ። ክብሬ ባላት ሀገሩ የገጠመው መከራ ደግሞ ሊሸከመው የማይችለው ነበር። በትውልድ መንደሩ ወገን ወገኑን እያሳደደ ሲደፋው ሲያይ፣ አንድ እግር ያሳጣው የኒዮ ናዚ ጉዳይ አላሳሰበውም። ወገን ሲጨንቀው ይሰደዳል። ታዲያ የትኛውን እንኮንን? የሳውዲውን? አ’ይ እሱ በራሱ ስራ ይጨነቅበት። የኛው ግን ሊያሳስበን ይገባል። ለም መሬታቸውን እየተቀራመቱ ማፈናቀላቸው ሳየንስ፤ ወጣቱ እንዳለው  ‘ከውጭ የገቡ እንግዶች መልሰው እኛኑ ባይተዋር እያደረጉን ነው።’

እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ በርካታ የኩባ ዜጎች የፊደል ካስትሮ መንግስትን በመቃውም ወደ አሜሪካ ገብተዋል።  አሜሪካ የገቡት ኩባውያን የካስትሮን መንግስት ከማውገዝ አርፈው አየውቁም ነበር። ካስትሮ ከ 20 አመታት በኋላ አሜሪካን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኙ፡ “የአሜሪካ መንግስት የኩባ ስደተኞችን መብት እየገፈፈ ነው።”  የሚል ወቀሳ ነበር ያቀረቡት። እናም በስደት ያሉ ኩባውያን መብት እንዲጠበቅ ከአሜሪካ መንግስት ጋር ድርድር ያዙ።  ካስትሮ እዚህ ላይ እንደግለሰብ ሳይሆን እንደመንግስት ነው የሚያስቡት።

የኛዎቹ ግን እንደመንግስት ሳይሆን አሁንም እንደግለሰብ ነው የሚያስቡት። በጅምላ የሚጠሉት ዲያስፖራ ላይ በቀላቸውን እየተወጡ ያሉ ይመስላል። ዛሬ በውጭ ያሉ ወገኖች የሚጮሁትን ያህል እንኳን በስልጣን ላይ ያሉት ድምጻቸውን ቢያሰሙ ኖሮ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው በደል እዚህ ደረጃ ላይ አይደርስም ነበር።

እንደ ሉአላዊ አካል የሚያስብ ብሄራዊ መንግስት እስኪኖረን ድረስ አሁንም የታማኝ በየነን ፈለግ ተከትለን ለወገኖቻችን መጮህ ግድ ይለናል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሳዑዲ አረቢያ እየተፈጸመ ያለውን ግድያን አስመልክቶ በአ.አ ሰልፍ መውጣትን አልደግፍም አለ

“በዜጎቻችን ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም” –  ሰማያዊ ፓርቲም ‹ከእናንተ በፊትም ሌሎች ዜጎች ደብዳቤ ይዘው መጥተው ተከልክለዋል ስለዚህ ለእናንተም አይቻልም›አቶ ማርቆስ ብዙነህ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ደብዳቤውን አቶ ማርቆስ ቢሮ አስቀምጠው ወጥተዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ አርብ ከ5.30 ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ በር ላይ የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ ዛሬ ጠዋት 4 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ለማስገባት የሄዱ ቢሆንም ደብዳቤውን የተቀበሏቸው የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር አቶ ማርቆስ ብዙነህ ‹ከእናንተ በፊትም ሌሎች ዜጎች ደብዳቤ ይዘው መጥተው ተከልክለዋል ስለዚህ ለእናንተም አይቻልም›በማለት ላለመቀበል ቢያንገራገሩም አመራሮቹ በቁርጠኝነት ደብዳቤውን አቶ ማርቆስ ቢሮ አስቀምጠው ወጥተዋል፡፡ አቶ ማርቆስ ብዙነህም ከንቲባው ከሰአት ስለሚገቡ እሳቸው ካልፈቀዱ ቀሪ ደብዳቤ ላይ አልፈርምም ቢሉም ሰማያዊ ፓርቲ አዋጁ በሚያዘው መሰረት ከ48 ሰአት በፊት የማሳወቅ ስራውን ጨርሶ በፅ/ቤቱ ለተቃውሞ እንቅስቃሴው ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል፡፡

semayawi part addis ababa saudi arabia

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)በሳውዲ አረቢያ በዜጎች ላይየሚፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት አውግዞ በቅርቡ በሚጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል በመቃወም ድምፁን እንደዲያሰማና ወገናዊ አጋርነቱን እንዲያሳይ መድረክ ጥሪ አቀረበ።

የሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ኢሰብኣዊነት አጥብቀን እናወግዛለን!!!

መድረኩ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ህዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን!

ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የተሰጠ መግለጫ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ድብደባ፣ ግድያና በጅምላ ማጎር ከኢሰብአዊነቱም በላይ የሳውዲ መንግስት ለዜጎች ያለው ክብር በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳፍር ድርጊት ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነት ክብር ላይ የተሰነዘረ ጥቃትም ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ሉአላዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ሲሆን ዜጎቻችን በጭካኔ ሲገደሉ፣ ሲፈነከቱ ሲታጎሩና ሲገረፉ ማየት አንገት ያስደፋል፡፡ በአንድ አፋኝ ስርዓት ውስጥ የምንገኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በላይ ምን እንላለን? ይህ በሳውዲ መንግስት ደፋርና ኋላ ቀር የሆነ ድርጊት የኢህአዴግን መንግስት የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ መፍጠር ድክመት ከመግለፁም በላይ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያለውን ደንታቢስነት ይመሰክራል፡፡ ድሮስ በመልካም አስተዳደር እጦት ፍትህን ከተነፈገ፣ በሙስና ከተጨማለቀና በፖለቲካ ስልጣን ለመቆየት ቆርጦ ከተነሳ የስልጣን ኃይል ምን ይጠበቃል? ዜጎችንና ሃገሪቱን ያስደፍደራል፣ የሉኣላዊነትን ክብር ያስነካል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት የተሳሳተ ፖሊሲ እየፈጠሩ ካሉት ችግሮች አንዱ ማህበራዊ ቀውስ መሆኑን ገጠዋል፡፡ ዜጎች ተስፋቸው ጨልሞ እየታያቸው ነው፡፡ ተስፋ ያጣ ዜጋ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በተወለደበት ቀየና ሃገር የኑሮ እምነትና ዋስትና የሌለው ዜጋ ሞት እየሸተተውም ይሰደዳል፡፡ በአገራችን ስራ አጥተው ስራ ፍለጋ ሲንከራተቱ በሰው ሃገር በረሃ ሰብአዊ ክብራቸው ተዋርዶ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎችን ዜና መስማት በኢህአዴግ አገዛዝ የተለመደ ሆኖአል፡፡ በጣም የሚያሳፍረው ኢህአዴግ እነዚህን ዜጎች “ህገ ወጥ ስደተኞች “ በሚል ፍረጃ ለመብታቸው ለመቆም ቁርጠኝነት የሚጎድለው መሆኑም ጭምር ነው፡፡ መድረክ ዜጎቻችን የሚሰደዱበት የተሻለ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ፍትህ ፍለጋ እንዲሁም አሰቃቂ የሆነውን የአንድ ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ ፓርቲ የፖለቲካ አስተዳደር ሽሽት መሆኑን ይገነዘባል፡፡ በተደጋጋሚ እንደገለፅነው ዜጎቻችን ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ ለመሰደድ በባህር፣ በበረሃና በጫካ ውስጥ ተቀጥፈው ቀርተዋል፡፡ የዚህ አንገት አስደፊ ዜና ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ እንጂ ሲቀንስ አይታይም፡፡ በለስ ቀንቷቸው ባህሩን፣ በረሃውንና የዱር አውሬውን አልፈው ማረፊያዬ ብለው ያሰቡበት አገር የሚደርሱትም ሌላ ግፍና በደል ይጠብቃቸዋል፡፡ ሃገራዊ ውርደትና ሞት ከተበላሸ ስርዓትና ፖሊሲው የሚፈጠር እንደመሆኑ የችግሩ ምንጭ ኢህአዴግ መሆኑን እናምናለን፡፡ መድረክ ይህ ሁሉ ውርደት የሚደርቀው የችግሩ ምንጭ ሲነጥፍ ነው ብሎ ያምናል፡፡ የችግሩ ምንጭ ደግሞ ኢህአዴግ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ፓርቲና መንግስት ላይ ህገ – መንግስታዊና ሰላማዊ የሆነ ተፅኖ በመፍጠር ስርአቱን መቀየር ወሳኝ መሆኑን ያምናል፡፡ ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር በጋራ እንዲንቀሳቀስ ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል፡፡ በሳውዲ አረቢያ የመንግስት ኃይሎች በዜጎቻችን ላይ በተፈፀመው ሰብአዊነት የጎደለው ድርጊት ላይ የመድረክ አቋም፡- – በዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ እንዲቆም፤ – ለተፈፀመው አስነዋሪ ወንጀል ተጠያቂው አካል ተለይቶ ለህግ እንዲቀርብ፣ ለተጎጂዎችም ካሳ እንዲከፈል፤ – ለተፈናቀሉ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታና መስራት የማይችሉት ተለይተው በክብር ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ፡፡ መስራት የሚችሉና ፈቃድ የሚያገኙቱ ሰብአዊ ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ እንዲረግ፤ – የኢህአዴግ መንግስት በጉዳዩ ላይ ለሕዝብ ሰፊ ማብራሪያ እንዲሰጥና ከሳውዲ መንግስት ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት በመፈተሽ ጠበቅ ያለ አቋም እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡ በዚህ ድርጊት መባባስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና በሳውዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር /ቆንስላ ጽ/ቤት ተጠያቂዎች ሲሆኑ ይህም ስልጣን የሚሰጠው – በችሎታና ለወገን ባለው ተቆርቋሪነት ሳይሆን በፓርቲ ታማኝነት እንደሆነ እየመሰከረ ያለ ጉዳይ መሆኑን ነው፡፡ አለምአቀፍ የሰብአዊና የዲሞክራሲ ተቋማትም ይህን አሳፋሪ ተግባር ህግና መንግስት ባለበት አገር እየተፈጠረ መሆኑን እንዲያስተጋቡ፡፡ ጉዳዩን ለአለም እያደረሱ ያሉትን ታላላቅ ሚዲያዎችን በዚሁ አጋጣሚ ለማመስገን እንወዳለን፡፡ መድረክ ድርጊቱን ለመኮነን በቅርቡ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግና ለማስተባበር ወስኗል፡፡ ቀኑን በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚያሳውቅ ሲሆን አጠቃላይ ሕዝቡ፣ ደጋፊዎችንና አባላት፣ በአገር ውስጥ የምትገኙ የተቃውሞ ጎራው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ነፃ ነን የምትሉ የሲቪክ ማህበራትና የኢህአዴግ አባላት ሁሉ በሚገለጸው ዕለት፣ ቦታና ሰዓት በመገኘት ድርጊቱን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ለማውገዝ ትገኙልን ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ኅዳር 04 ቀን 2006 ዓ.ም

Posted by Hellen Tesfaye

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ:

 

 
ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ: ተቀባይነት አላገኘም::#Ethiopia ሕወሓት ለወይዘሮ አዜብ ስልጣን በመስጠት በስልት ልታጠምዳቸው ነው::#TPLF
“ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው::” የሚሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት የሆኑት እና የሙስናዋ ወይዘሮ በመባል የሚታወቁት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለፓርቲያቸው ያቀረቡት የፖለቲካ በቃኝ ማመልከቻ ተቀባይነት ማጣቱ ሲገለጽ የሕወሓት ከፍተኛ ሰዎች ወይዘሮ አዜብን ለማጥመድ በሚያስችል ስልጣን ላይ ሊያስቀምቷቸው እንዳሰቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል::የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው በወይዘሮ አዜባ ጋር በዋዛ አንላቀቅም በማለት ቂም በቀላቸውን ሊወጡባቸው ይችላሉ የሚል ግምቶች በሕወሓት አከባቢ እየተነገሩ ነው::
ለወይዘሮ አዜብ የታሰበው ስልጣን የትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በስልት ከፖለቲካ ለማፈግፈግ እና ለመልቀቅ ከአገር ለመውጣት እንደማይቻል ተነግሯቸዋል:: ወይዘሮ አዜብ በድጋሚ ማመልከቻ ማቅረባቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ምንጮቹ ምንኛውም ስልጣን ቢሰጣቸው በአዲስ አበባ መስተዳደር ምክር ቤት ውስጥ አባል ሆነው የመቀጠል ፍላጎት እንዳሌላቸው በግልጽ ተናግረዋል::ባልቤቴ ከሞተ በኋላ በሕወሓት ተገፍቻለሁ የሚሉት ወይዘሮ አዜብ ምንም ነገር ሊመቻቸው እንዳልቻለ እና ስለ እሳቸው ውስጥ ለውስጥ የሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች እያበሳጯቸው እንደሆነ ተናግረዋል በተጨማሪም ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው ሲሉ አማረዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ.
Posted by Hellen Tesfaye

ዶላር ለመሰብሰብ ወደ ሙኒክ ያቀናው የህወሀት ቡድን አልቀናውም

 

በአባይ ግድብ ስም ቦንድ በመሸጥ ጠቀም ያለ ዶላር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ጀርመን፣ ሙኒክ ከተማ የተንቀሳቀሰው የህወሀት/ኢህአዴግ መልዕክተኛ ቡድን ከኢትዮጵያውያን የደረሰበትን ከፍተኛ ተቃውሞ መቋቋም ሳይችል ቀርቶ ያሰበውን ዶላር ሳይሰበስብ ቀርቷል።

ኢትዮጵያውያኑ የእለቱ መሪ መፈክራቸው አድርገውት የዋሉት እየተለመደ የመጣውን “ወያኔ ሌባ” የሚለውን መፈክር ሲሆን የታሰሩ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞችም እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ቀደም ሲል የህወሀት/ኢህአዴግ ቡድን የቦንድ ሽያጩን ሊያከናውን አቅዶ ከነበረበት የሆቴል አዳራሽ ባለቀ ሰዓት ተባሮ ነው ዛሬ ኢትዮጵያውያኑ ተቃዋሚዎች ተቆጣጥረውት የዋሉትን አዳራሽ እመንደር ውስጥ ሊከራይ የተገደደው።

የህወሀት መልዕክተኞች ይዘውት የነበረውን የሆቴል አዳራሽ ሊለቁ የተገደዱበት ምክንያት በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአዳራሹን ባለቤቶች በኢሜል እና በፋክስ ከወንጀለኛ ቡድን ከህወሀት ጋር የተፈጸ ውል ስለሆነ እንዲፈርስ በመጠየቃቸው መሆኑ ታውቋል።

Posted by Hellen Tesfaye

“ከ6 ሚሊዮን የኢህአዴግ አባል አንዱ ብሆን ምን ችግር አለው?” አቶ ልደቱ አያሌው

 “ከ6 ሚሊዮን የኢህአዴግ አባል አንዱ ብሆን ምን ችግር አለው;” “ወ/ት ብርቱካን የተሰጣት ኃላፊነት አግባብ አይደለም” “እንባ አውጥቼ አልቅሼ ኃላፊነት በቃኝ እያልኩ ነው የተመረጥኩት” “ከኢንጂነር ኃይሉ እንዲሕ ያለ ውሸት አልጠብቅም ነበር”

“የእስክንድር ነጋ ጋዜጣ ቅንጅትን ወደተሳሳተ አቅጣጫ ገፍቷል”

– አቶ ልደቱ አያሌው

lidetu
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው መውጣት የጀመሩት በ1990ዎቹ ሲሆን፣ ከምርጫ 97 ዋዜማ አንስቶ አነጋጋሪነታቸው በእጅጉ ጨምሯል፡፡ ከሁለት ዓመት የእንግሊዝ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱት አቶ ልደቱ አያሌው ጋ፣ የሎሚ መፅሔት አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡-
ሎሚ፡– ለረዥም ጊዜያት ከሚዲያም ከፖለቲካም ርቀኻል፤ በሠላም ነው?
ልደቱ፡- እንደሚታወቀው ሀገር ውስጥ አልነበርኩም፡፡ በኢዴፓ ውስጥ የነበረኝን የሥራ አስፈፃሚ ኃላፊነትም አስረክቤ ስለነበር ወደ ሚዲያ የምመጣበት ዕድል አልነበረም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፖለቲካችን ወደተስተካከለ መስመር ለመግባት ስለተቸገረ፤ አንዳንድ ጊዜ ለሀገር፣ ለሕዝብ ይጠቅማል ብለህ የምትሰራውና የምትናገረው ነገር በሌሎች ዘንድ ትርጉሙ እየተለየ ሲያስቸግር፣ ሰዎች በነገሮች ላይ የማሰቢያ ጊዜ እንዲያገኙ ፋታ መስጠትም ይጠቅማል ብዬ ነው፡፡ እንጂ ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለም፡፡
ሎሚ፡- ከፓርላማ የአምስት ዓመት ቆይታህ በኋላ የነበረው ጊዜህን በምን ነበር ያሳለፍከው?
ልደቱ፡- ፓርላማ አምስት አመት ነው የቆየሁት፡፡ የፓርላማው አሠራር በሚፈቅደው መሠረት እንደ ፓርቲያችንን ወክለን ተሣትፎ ስናደርግ ነበር፡፡ በተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥም የተወከሉ ነበሩ፡፡ ከኛ ፓርቲ አቅማችንና ሁኔታው በፈቀደው መጠን ለነዛ ኮሚቴዎች ገንቢ የሆነ ተሣትፎ ለማድረግ ጥረት አድርገናል፡፡ እኔም እንደ ሕዝብ ተወካይነቴ ክርክሮችና ውይይቶች ሲኖሩ የራሴን ዝግጅት አድርጌ ከፓርቲያችን አቋም አንፃር ሃሣቡ ተቀባይነት ያግኝም አያግኝም የሚታየኝን፣ የሚመስለኝን አቋም በማራመድ በጐ ተሣትፎ አድርጌያለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ከሞላ ጐደል ጠቃሚ ተሣትፎ ነበረን ብዬ አምናለሁ፡፡ እኛ ፓርላማ ብንገባም ባንገባም፣ የተቃዋሚው ጎራ በአብዛኛው ወይም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከፓርላማ መውጣቱ ያሳዝነኛል፡፡ ይህ ሂደት ተጠናክሮና ጐልብቶ ፓርላማችን የተለያዩ አስተሳሰቦች የሚንፀባረቁበት መድረክ ሆኖ የሚቀጥል መስሎኝ ነበር፡፡ አለመታደል ሆኖ ወደኋላ ነው የሄድነው፡፡
ሎሚ፡- በርካታዎች በምርጫ 97 ሠሞን ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ይመጣል ብለው ይገምቱ ነበር፤ አንተስ?
ልደቱ፡– Well እንግዲህ፡፡ በ1997 ዓ.ም. ለውጥ ለማምጣት አንድ ዕድል ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ግን መጀመሪያ ለውጥ ማለት ምንድነው? በሚለው መስማማት አለብን፡፡ ምናልባት ለውጥ ለማምጣት 97 ላይ ዕድል ነበር ሲባል አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት መንግስታዊ ለውጥ ማምጣት ከሆነ የተለየ ነው፡፡ እኔ በዚህ በኩል ብዙ ዕድል ነበር ብዬ አላምንም፡፡ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታው ገንቢ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ከሆነ እስማማለሁ፡፡ ሰዎች ለውጥን የሚያዩበት መንገድ ይለያያል፡፡

ለእኔ 1997 ዓ.ም. የመንግስት ለውጥ የሚመጣበት ጊዜ አልነበረም፡፡ ያን ደግሞ የምናውቀው ምርጫ ውስጥ ከገባን በኋላ ሳይሆን ወደ ምርጫ ለመግባት ዝግጅት ስናደርግ ነው፡፡ ይህንንም በኢዴፓ ደረጃ ተወያይተንበት፣ ነባራዊ ሁኔታውን ገምግመን የያዝነው ጉዳይ ነበር፡፡ “…በዚህ ምርጫ አሸንፈን አዲስ አበባ ከተማን እንቆጣጠራለን፤ በቂ የሚባል የፓርላማ መቀመጫ  እንይዛለን፤ ይሄን ውጤት ይዘን ከአምስት አመት በኋላ በሚደረግ ምርጫ ደግሞ መንግስት ለመሆን የሚያስችለንን ዕድሉን እናገኛለን” ብለን ነው ተሳትፎ ያደረግነው፡፡

በምርጫ ስትሣተፍ “አሸንፋለሁ” እያልክ ነው መቀስቀስ ያለብህ፡፡ ይህ የግድ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ግን በውስጣችን ከነበረው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በ97 መንግስት ለመለወጥ የሚያስችል ሁኔታ አልነበረም፡፡ አንድ ቀላል ምሣሌ ላንሳ፤ ቅንጅት በዚያ ምርጫ ከባድ ተፎካካሪ ሆኖ ነው የቀረበው፡፡ ግን በ130 ወረዳዎች ተፎካካሪ አላቀረብንም፡፡ ይሄ በራሱ ሙሉ ለሙሉ እንዳናሸንፍ ያደረገ አንድ ችግር ነበር፡፡

lidetu-ayalew-and-muse-semuበወቅቱ እኛ ብቻ አልነበርንም በተቃዋሚነት ምርጫ ፉክክር ውስጥ የገባነው፡፡ “ህብረት” ውድድር ውስጥ ነበር፤ እኛና ህብረቱ የምንካፈለው የሕዝብ ድምፅ ነበር፡፡ ሁለታችን ለየብቻ ስለተወዳደርን የተቃዋሚውን ድጋፍ ለሁለት እንካፈለዋለን፡፡ ይህ ደግሞ ኢህአዴግ በብዙ ቦታዎች ላይ በአነስተኛ ድምፅ የሚያሸንፍባቸውን ሁኔታዎች ፈጥሮ ነበር፡፡ ሌላው እንደተቃዋሚ ብዙ ያልሰራንባቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ፡፡ ቅንጅቱን እንደ ነፍጠኛ እና እንደ አማራ ኃይል የሚያይና በኢህአዴግ ተጠቃሚ ነኝ የሚል ክፍል ነበር፡፡ እነዚያ የሕብረተሰብ ክፍሎች እኛን እንደማይመርጡ ግልፅ ነበር፡፡

ምርጫው ግልፅና ፍትሃዊ እንደማይሆንም ቀድመን እናውቅ ነበር፡፡ ለምሣሌ ወደ 905 ሺህ ሰው በታዛቢነት ማቅረብ ነበረብን፡፡ እኛ ያቀረብነው 15 ሺህ ታዛቢ ነው፡፡ ይህ የሚያሣየው ወደ 85 ሺህ ታዛቢ ልናቀርብበት የምንችልበት ቦታ ክፍት መሆኑን ነው፡፡ በኒዚያ ቦታዎች የማጭበርበሩን ሁኔታ ማስቀረት ይቅርና ታዛቢ ባቀረብንባቸው ቦታዎች እንኳን ምርጫው ስለመጭበርበሩና አለመጭበርበሩ መረጃ ልናቀርብ የምንችልበት ዕድል አልነበረም፡፡ ታዛቢ አጥተን ያላቀረብንበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ ከነዚህ አጠቃላይ ሁኔታዎች አንፃር በ97 ምርጫ ለውጥ ለማምጣት ዕድል አልነበረም፡፡

ሎሚ፡- አሁን ከዘረዘርካቸው ምክንያቶች በተጨማሪ በምርጫ 97 የተቃዋሚዎችን ዕድል ያጨናገፈው አቶ ልደቱ አያሌው መሆኑ ይነገራል፤ አሁን ላይ ሆነህ ምን ምላሽ ትሰጣለህ?

ልደቱ፡- ይባላል! በነገራችን ላይ ለዚህ ጥያቄ ብዙ ጊዜ መልስ ሰጥቻለሁ፡፡ መሠረት የሌለው ጥያቄ ነው፡፡ አሉባልታ ነው፡፡ ተጨባጭ ነገር አይደለም፡፡ ግን ዞሮ ዞሮ ደጋግሞ ይመጣብሀል፡፡ እኔ ስለ አሉባልታ ማውራት ትቻለሁ ብቻ ሳይሆን ተጠይፌያለሁ፤ አንገፍግፎኛል፡፡ ግን አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ወይም አንዳንድ ድርጅቶች በሃሣብ ደረጃ ስትሞግታቸው መልስ የሚሰጡህ በሀሣብ አይደለም፡፡ በአሉባልታ ነው፡፡ ስለዚህ ያን ለማስተባበል አንተም አሉባልታ ማፍራት ትጀምራለህ፡፡ ሁሉም ይቆሽሽና ፖለቲካው አስቀያሚ ይሆናል፡፡

ጥያቄውን ለመመለስ ያነሳኸው ጉዳይ ሲባል እሰማለሁ፤ ቅንጅትን ልደቱ አፈረሰው ይባላል፡፡ እንደዚህ የሚሉ ሰዎች አንዳች ተጨባጭ መረጃ የላቸውም፡፡ እኔ አንድ ግለሰብ ነኝ፡፡ ቅንጅት የአራት ፓርቲዎች ውህደት ወይም ጥምረት ነው፡፡ አንድ ግለሰብ ቅንጅትን ባሻው ጊዜ፣ በራሱ ፍላጐትና እምነት ተነስቶ የሚያፈርስ ከሆነ ምን ዓይነት ቅንጅት ነበር?… የአራት ድርጅቶች ሕብረት አልነበረም ማለት ነው፡፡ እኔ ስፈልግ የማፈርሰው ከሆነ ደግሞ ራሴ ብቻዬን ቅንጅት ነበርኩ ማለት ነው፡፡

ሰዎች ለቅንጅት ያላቸው አመለካከት የተለየ ነበር፡፡ በጣም ጠንካራና ግዙፍ አካል አድርገው ነበር የሳሉት፡፡ በሌላ በኩል ያን አግዝፈው የሳሉትን ቅንጅት “ልደቱ” የሚባል አንድ ግለሰብ አፈረሰው ይላሉ፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ አይደለም ልደቱ፣ ኢዴፓ የሚባል ፓርቲ ቅንጅትን ሊያፈርሰው አይችልም፡፡ ምክንያቱም የአራት ፓርቲዎች ጥምረት ነውና፡፡ ከአራቱ ፓርቲዎች አንዱ ፓርቲ ፍላጐት ሣይኖረው ቢወጣ ሦስቱ ፓርቲዎች ቅንጅት ሆነው መቀጠል ስለሚችሉ ሊያፈርሰው የሚችል ምክንያት የለም፡፡ አንድም ቀን “ቅንጅት የኛ ቅንጅት ሆኖ አይቀጥልም” ብለን ክስ አቅርበን አናውቅም፡፡ መስማማት ከቻልን በጋራ መቀጠል እንችላለን፤ ካልቻልን ግን እኛን ተዉንና እናንተ ቀጥሉ ነው ያልነው፡፡

ሦስቱ ድርጅቶች ቅንጅት ሆነው መቀጠል ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ አሉባልታው ምንም መሠረት የለውም፡፡ አንዳንድ ሰው ልደቱ ያፈረሰው ሊመስለው ይችላል፡፡ በሆነ አጋጣሚ የተወሩትን አሉባልታዎች መሠረት አድርጐ ወይም ከቅንጅት አገኘዋለሁ ብሎ የነበረውን አጉል ተስፋ ሲያጣ ጥፋቱን የሆነ አካል ላይ ወርውሮ በእከሌ ጥፋት ነው ቅንጅት የፈረሰው ሊል ይችላል፡፡ አልፈርድም! ሰው ብዙ ተስፋ አድርጐ ነበር፡፡ ያንን ተስፋ ሲያጣ፣ ተስፋ የጣለበትን ምክንያት የሆነ አካል ላይ መወርወር ነበረበት፡፡ ስለዚህ እኔ ላይ ወረወረው፡፡ ችግሩን ልረዳ እችላለሁ፡፡

ቅንጅትን በማፍረስ ረገድ ሚና ካለኝ እኔ ከቅንጅት ተለየሁ አይደል?… የቅንጅት አመራሮች እስር ቤት ገቡ፤ ከሁለት አመት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ወጥተው አንድ ላይ መስራት ጀመሩ፡፡ ችግሩ እኔ ከሆንኩ እኔ በሌለሁበት ቅንጅት ጠንካራ ሆኖ መቀጠል ነበረበት፡፡ ግን ቀጠለ?… የቅንጅት አመራሮች ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ አብረው መስራት ቢጀምሩም ወደ ስምንትና ዘጠኝ ቦታ ከመከፋፈል አልዳኑም፡፡ ስለዚህ ቅንጅትን ያፈረሰው ልደቱ አልነበረም፤ የማፍረስ አቅምም አልነበረውም፡፡ ቅንጅት የፈረሰው በራሱ ውስጣዊ ድክመት ነው፡፡ እኛ ፓርላማ እንግባ ነው ያልነው፡፡ አዲስ አበባን ያኔ ተቀብለን ይዘን ቢሆን ኖሮ አሁን ያለው የትግል ሁኔታ በጣም የተለየ ይሆን ነበር፡፡

ሎሚ፡- በወቅቱ የያዛችሁት አቋም “እውነተኛውን ዴሞክራሲ መፍጠር” የሚል ነበር፤ በዚህ መንገድ እየተጓዛችሁ ሳለ አንተ ግን ቅንጅት ሲዋሃድ የሥልጣን ጥያቄ ማቅረብሕና በኋላም ማኩፈፍህ ነበር የተነገረው፤ ይህ ለምን ሆነ;

ልደቱ፡- ልደቱ “ስልጣን ይገባኛል ብሎ ነበር” ብሎ በመረጃ አስደግፎ የሚመጣ ሰው ካለ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ እኔ ኃላፊነት መውሰድ እችላለሁ፡፡ በነገራችን ላይ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ገብተህ የስልጣን ጥያቄ ማቅረብ ስህተትም ወንጀልም አይደለም፡፡ ፖለቲካ የስልጣን ጥያቄ ነው፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ እኔ በኢዴፓ/መድህን ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ሰባት አመታት ሳልፈልግ ተመርጬ ነው አመራር የሆንኩት፡፡ ሳልፈለግ ስልህ አልፈልግም ብቻ ሣይሆን በአንደኛው ጉባኤ እንባ አውጥቼ አልቅሼ ኃላፊነት በቃኝ እያልኩ ነው የተመረጥኩት፡፡

በኋላ በነበሩት ሂደቶች ኢዴፓ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ፣ ችግር ላይ ስለነበር የአመራርነቱን ሚና ትቼ መሄድ አልፈለግኩም፡፡ ፈልጌም ነው የተመረጥኩት፡፡ በተለይ ደግሞ የቅንጅት አመራር ሆኜ ስመረጥ የመመረጥ ፍላጐት አልነበረኝም፡፡ እንባ አውጥቼ መድረክ ላይ ወጥቼ ለምኛለሁ፡፡ እምቢ ተብዬ ነው የሆንኩት፡፡ ቅንጅት ውስጥ እያለሁ ከኃላፊነቴ ለመልቀቅ ሦስት ጊዜ መልቀቂያ አቅርቤያለሁ፡፡ የኃላፊነት ፉክክር ውስጥ አንድም ቀን ገብቼ አላውቅም፡፡

ሎሚ፡- ኢንጂነር ኃይሉ ከሥልጣን ወርደው አንተ ለመሾም ጥያቄ አላቀረብክም?

ሰሞኑን ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ያወጡት መፅሐፍ ላይ “ልደቱ እጁን አውጥቶ ኢ/ር ኃይሉ ሻውልን ከስልጣን አውርዳችሁ እኔን ሊቀመንበር አድርጉኝ” ብሏል ብለው መፃፋቸውን ሰምቻለሁ፡፡ በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ በቅንጅት ውስጥ ብዙ ሰዎች ነው የነበሩት፡፡ ኢ/ር ኃይሉ ያሉት “እውነት ነው ውሸት ነው” ማመዛዘን የሚችልና ህሊና ያለው ሰው ሊፈርድ ይችላል፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ መድረክ ላይ እጁን አውጥቶ እከሌን አውርዱትና እኔን ሹሙኝ ብሎ አይጠይቅም፡፡ በፍፁም እንደዚህ ዓይነት ነገር አድርጌ አላውቅም፡፡ ተመኝቼውም አላውቅም፡፡ ቅንጅት ውስጥ በነበረው ሂደት ያለመመረጥ፣ ስልጣን ያለመያዝ ፍላጐት ነው የነበረኝ፡፡

ምናልባት ፕ/ር መስፍን በጋዜጣ ፅፈውት አንብበህ ሊሆን ይችላል፤ “ልደቱ ሁልጊዜ መመረጥ የሚፈልገው ቤቱ ቁጭ ብሎ ነው፤ ሎቢ ማድረግ አይፈልግም” ብለው ነው የተናገሩት፡፡ እኔ በትግሉ ውስጥ ተሣትፎ ማድረግና የሚገባኝን ስራ መስራት ነው የምፈልገው እንጂ ስልጣን መያዝ አይደለም፡፡ ነገሮች ከአንዱ ወደ ሌላው እየዘለሉ ከአቅሜ በላይ በሆነ ምክንያት “ታስፈልገናለህ” እየተባልኩ ነው ስመረጥ የነበረው፡፡ ብጠይቅ ችግር ነው፣ ስህተት ነው እያልኩ አይደለም፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ጠይቄ አላውቅም፡፡ አንተ ጋዜጠኛ ነህ፤ የቅንጅት አመራር የነበሩ አራት አምስት ሰዎችን ጠይቀህ፣ ሁለትና ሦስት ሰዎች “ልደቱ የሥልጣን ጥያቄ ነበረው” ካሉህ እኔ ተሳስቻለሁ ማለት ነው፡፡ ይቅርታም እጠይቃለሁ! ሊሉህ እንደማይችሉ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ እንግዲህ እኚህ ሰውዬ ትልቅ ሰው ናቸው፤ አቋማቸው ይጣመኝም አይጣመኝም ትግሉ ውስጥ ለከፈሉት ዋጋ አክብሮት አለኝ፡፡ ግን እንደዚህ ዓይነት ውሸት አልጠብቅም ነበር፡፡ ቅንጅትን ስንመሰርት ሊቀመንበር ሆኖ የመቀጠል ዕድል ነበረኝ፡፡ ግን “አይሆንም፤ የበሰሉ ሰዎች ቢመሩት ይሻላል” ብለን ነው ዶ/ር ኃይሉ እና ዶ/ር አድማሱን ከቤታቸው አምጥተን ስልጣኑን እንዲይዙትና እኛ የበታች ሆነን እንድንሰራ ያደረግነው፡፡ ይህንንም በተግባር አሳይተናል፡፡

ሎሚ፡- ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የቅንጅት ም/ሊመንበር ሆና ስትመረጥ፣ አንተ ለቦታው ራስህን አጭተህ ስለነበር በእጅጉ መበሳጨትህ ተሰምቷል፤ ይሕ ደግሞ በአንድ ሰው የተገለፀ ሳይሆን በርካታ የቅንጅት አመራሮች በተለያየ አጋጣሚ ደጋግመው የገለፁት ነው፤ ሥልጣን ካልፈለግክ ምን ነበር ያበሳጨህ;

ልደቱ፡- ቅድም እንዳልኩት ሰዎች እንዲሕ ሊሉ ይችላሉ፡፡ የሆነውን ነገር ግን ልነግርህ እችላለሁ፡፡ ወ/ት ብርቱካን በቅንጅት ውስጥ የተሰጣት ኃላፊነት አግባብ ነው ብዬ አላምንም፡፡ እንድትመረጥ የተደረገው በድርጅታዊ አሠራር መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ወ/ት ብርቱካን ወደ ትግል እንድትመጣ ከማንም በላይ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ እንደውም መመረጧ ደስ ብሎኝ በግንባር ቀደምነት ነው “እንኳን ደስ ያለሽ” ያልኳት፡፡ መድረክ ላይ የሆነው ይሄ ነው፡፡ የተወራው ደግሞ ሌላ ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡ እየተዳኘሁ ያለሁት በምሰራው ሥራ ወይም ባራመድኩት አቋም አይደለም፡፡ ሰዎች ስለኔ ባወሩት ወሬ ነው እየተዳኘሁ ያለሁት፡፡ ብርቱካን አልሞተችም አለች… እሷን ማነጋገር ትችላለህ፡፡

ሎሚ፡- ቅንጅት ውስጥ አለመግባባት በነበረበት ወቅት “የምሁራን ስብስብ ተፅዕኖ ሊፈጥርብን አይችልም” የሚል ንግግር ተናግረህ እንደነበር ታስታውሳለህ;

ልደቱ፡– አልገባኝም;…

ሎሚ፡- ወ/ት ብርቱካን እና ኢ/ር ኃይሉ ሻውል በቅንጅት አመራርነት ከተመረጡ በኋላ “የምሁራን ተፅእኖ ሊኖር አይገባም” ብለህ ነበር?…

ልደቱ፡- እንደዚያ ብዬ የተናገርኩበት ጊዜ አልነበረም፤ አላስታውስም፡፡ ግን በአጠቃላይ በሕይወትህ ምን ስህተት ሰርተሀል? ምን ዓይነት አመለካከት ነበረህ? ብትለኝ አንዱ ስህተት ለምሁራን የነበረኝ አመለካከት ነው፡፡ እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፕሮፌሰርን፣ ዶክተርን… የፖለቲካ ሊቅ አድርጌ ነበር የማየው፡፡ ለዚያም ነው ኢዴፓን ስንመሰርት እኛ መስርተን እኛው መምራት የለብንም ብለን ምሁሮችን ከቤታቸው አምጥተን ኃላፊነት ላይ ያስቀመጥነው፡፡ ምናልባት ባላጋንነው ምሁር የሆነ ሰው የሚዋሽ አይመስለኝም ነበር፡፡ የስልጣን ጥማት ያለው አይመስለኝም ነበር፡፡ ሀገር ወዳድ ይመስለኝ ነበር፡፡ ሃቀኛ ነበር የሚመስለኝ፡፡ ግን በጣም የተሳሳተ አመለካከት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ግን እንደዚህ አላስብም፡፡ ስለተማረና ስላልተማረ አይደለም፤ አንድ ሰው ምሁር ሆኖም የፖለቲካ ሴረኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ያልተማረም የፖለቲካ ሴረኛ አለ፡፡ በዚህ ረገድ ድሮ የነበረኝና አሁን ያለኝ አመለካከት ተቀይሯል፡፡ ግን አንተ እንዳልከው ቅንጅት ውስጥ ምሁራንን የተናገርኩበትን ጊዜ አላስታውሰውም፡፡

ሎሚ፡- ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር ተገናኝታችሁ ያወራችሁበት ጊዜ ነበር;

ልደቱ፡- ይመስለኛል፤ ሁለት ሦስት ጊዜ፡፡

ሎሚ፡– “እየሄድክበት ያለው መንገድ ጥሩ አይደለም፤ ለኢህአዴግ እየሰራህ ነው፤ ይህም ታውቋል፤ ስለዚህ ራስህን ከቦታው ብታገልል ጥሩ ነው” ያለህ ጊዜ ነበር;

ልደቱ፡- እስክንድር እንደዚህ ብሎኝ አያውቅም፡፡ ስለኔ ብዙ ነገር መፃፉን ግን አውቃለሁ፡፡ እስክንድር ፓርቲ አይደል መሪ አይደል፤ ከሂደቱ ውስጥ ውጣ አትውጣ ብሎ ሊያዘኝ የሚችልበት ምክንያት አይኖርም፡፡ እኔ እና እሱ በእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ዙሪያ አውርተን አናውቅም፡፡

ሎሚ፡-  ታዲያ “የአረም እርሻ” በሚለው መፅሐፍህ ውስጥ ሰፊ ቦታ ሰጥተህ ለምን ወቀስከው;

ልደቱ፡– ቅንጅት ውስጥ በነበርኩበት በተለይ ፓርላማ “ይገባ አይገባ” በሚባልበት ወቅት እሱ ያራምደው የነበረው አቋም ተገቢ አልነበረም፡፡ በእኔ እምነት ቅንጅትን ወደተሳሳተ አቅጣጫ እንዲሄድ ከገፉት መካከል አንዱ የእስክንድር ጋዜጣ ነው፡፡ በዛ ምክንያት በመጽፌ ተችቼዋለሁ፡፡ እሱ በየሳምንቱ ይተቸኝ አልነበር? ታዲያ እኔ ብተቸው ምን ችግር አለው?

ሎሚ፡- እሱ የተቸህ እኮ አንተ የቅንጅት አመራር ሆነህ “ከኢህአዴግ ጋር በጐን እየሰራህ ነው” ብሎ ነው…

ልደቱ፡- ይሕን ለኔ… ነግሮኝ አያውቅም፡፡ እስክንድር እንደ አንድ ጋዜጠኛ ወይም እንደ አንድ የጋዜጣ ባለቤት የነበረው አቋም ስህተት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እሱ በቅንጅት ውስጥ ያራምደው የነበረው አቋም ስህተት ነው ብሎ እንደሚያምነው፣ እኔም እሱ ያራመደው አቋም ስህተት ነው ብዬ ፅፌያለሁ፡፡ ይህ ችግር ያለው አይመስለኝም፡፡ በምትለው መልኩ ግን “ለኢህአዴግ እየሰራህ ነው” ብሎ የነገረኝ ጊዜ የለም፡፡

ሎሚ፡- ከቅንጅት ዕውቅና ውጪ ከአቦይ ስብሀት ነጋ ጋር የተገናኘኸው በምን ምክንያት ነው;

ልደቱ፡- የት ነው የተገናኘነው? አንተን ልጠይቅህ እስኪ፤

ሎሚ፡– በወቅቱ መረጃው የወጣው “መዝናኛ” በተሰኘ ጋዜጣ እንደሆነ አትዘነጋውም፤ ሁለታችሁ የተገናኛችሁትም በተጠቀሰው ዕለት ከቀኑ 11፡30 በኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ቢሮ ውስጥ መሆኑም ተገልጿል…

ልደቱ፡- ዞሮ ዞሮ ይሄ ወሬ በተወራበት ወቅት ከአቶ ስብሀት ጋር አልተገናኘሁም፡፡ ይሄ ጉዳይ ሲወራም አቶ ስብሀት የተባሉትን ሰው በዓይኔም አይቻቸው አላውቅም ነበር፡፡ እንደ ማንም ሰው መፅሔት ላይ ፎቶግራፋቸውን ከማየት ውጪ አቶ ስብሓት ነጋ ቀይ ይሁኑ ጠይም፣ ረዥም ይሁኑ አጭር አላውቅም ነበር፡፡

ሎሚ፡- ከአቦይ ስብሃት ጋ አልተገናኛችሁማ?

ልደቱ፡- ይሔ ወሬ ሲወራ አንተዋወቅም፡፡ አቶ ስብሀትን በአካል ያየኋቸው ወይም ያገኘኋቸው ይሄ ወሬው ከተወራ ከሁለት አመት በኋላ ይመስለኛል፡፡ የቅንጅት ችግር ከተፈጠረ ከሁለት ዓመት በኋላ ፈረንሣይ ኤምባሲ አንድ የኮክቴል ግብዣ ላይ ነው ያገኘኋቸው፡፡ ግን ያኔ በሆነ አጋጣሚ ተገናኝተን ቢሆን እንኳን ምንም የሚያሳፍረኝ ነገር የለም፡፡ ደስ የሚለኝ ነገር ነው፡፡ የሚያሳዝነኝ ግን የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች (በገዢውም በተቃዋሚም ያለነው) በሀገር ጉዳይ ላይ እየተገናኘን አለመነጋገራችን ነው፡፡

ሎሚ፡- አንዳንድ ምንጮች ልደቱን ብአዴን/ኢህአዴግ አስቀድሞ ያዘጋጀው ሰው ነው ይላሉ፤ ተቃዋሚ መስለሕ ለማደናገር ወደ ፓርቲዎቹ እንደገባሕም ይነገራል፤ ያንተ ምላሽ ምንድነው;

ልደቱ፡– አሁን ለዚህ መልስ ብሰጥህ ምን ጥቅም አለው?… ኢህአዴግ በዚያ ደረጃ አዘጋጅቶ ወደ ተቃዋሚ ጐራ ሰርጌ እንድገባ ያደረገኝ ሰው ከሆነ የምሰጠው መልስ ይታወቃል፡፡ አይደለሁም ነው የምልህ፡፡ ግን ኢህአዴግን ለመጥቀም ከተፈለገ ለምንድነው ተቃዋሚ ውስጥ የምገባው? ኢህአዴግ ተቃዋሚ በዝቶበት አይደል እንዴ የተቸገረው፡፡ እንደዚህ ብለው የሚናገሩ ሰዎች መረጃቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ኢህአዴግ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ አባላት አሉት፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ብሆን ችግር የለውም፤ መሆን ብፈልግ ማለት ነው፡፡ የሚያሣፍርም ነገር የለውም፡፡ የኢህአዴግን የፖለቲካ አመለካከት አልወደውም፣ አላምንበትም እንጂ ባምንበት እኮ ኢህአዴግ እሆናለሁ፡፡ የሚያሳፍር ነገር አይደለም፡፡ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ብዙ ጓደኞች አሉኝ፤ ወንድሞች እህቶች አሉኝ፡፡ ግን አጋጣሚ ሆኖ የኔና የኢህአዴግ የፖለቲካ አመለካከት ስለማይጣጣም አልሆንኩም፡፡

ሎሚ፡- ቅንጅት በአንተ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ ወስዶ ነበር፤ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ስትገቡ ፍተሻው ሁሉንም የሚያካትት ቢሆንም መንስዔው ግን የአንተ ተጠርጣሪነት ነበር…

ልደቱ፡- ስለጉዳዩ ላስረዳህ፤ ፍተሻ ነበር፡፡ ያ የሆነው የቅንጅት አመራር የሚነጋገርባቸው አጀንዳዎችና ቃለ ጉባኤዎች በማግስቱ “ኢፍቲን” በሚባል ጋዜጣ ይወጣ ስለነበረ ነው፡፡ በኋላ ላይ በስልክ ወይም በዘመናዊ መሣሪያ የሚቀርፅ ሰው አለ ተባለ፡፡ ሁላችንም ሞባይላችንን ውጪ እየተውንና እየተፈተሽን እንግባ ብለን ተነጋግረን ወሰንን፡፡ ሞባይላችንን ውጪ እያስቀመጥን እየተፈተሽን መግባት ጀመርን፡፡ እንግዲህ በዚያ ጊዜ የሚጠረጠሩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እኔ ግን በተፈጠረው አለመግባባት መልቀቂያ ጠየቅኩኝ፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ ያንን ፊርማ ከፈረመ በኋላ ከሕዝብ ግንኙነት ኃላፊነቴ ለቀቅኩ፡፡ እኔን ተክቶ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ገባ፡፡ ከአመራር ውስጥ ወጣሁ፡፡

ከወጣሁ በኋላም “ኢፍቲን” ጋዜጣ ያንን ነገር መዘገቡን ቀጠለ፡፡ ፍተሻውም ይካሄዳል፡፡ እኔ ብሆን ኖሮ እኔ ስወጣ መቆም ነበረበት፡፡ ግን ቀጠለ፡፡ ቃለ ጉባኤ የያዝንበት ምስጢር እየወጣ ስንቸገር እስቲ አንዳንድ ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮችን ሌሎቻችን በሌለንበት አራቱ የድርጅት መሪዎች ለብቻቸው ይነጋገሩ አልን፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ አራቱ የድርጅቱ መሪዎች (ዶ/ር ብርሃኑ፣ ዶ/ር አድማሱ፣ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል እና ዶ/ር አለማየሁ) ሰሜን ሆቴል ስድስተኛ ፎቅ አጀንዳ ይዘው ውይይት አደረጉ፡፡ አራቱ ብቻ ናቸው የተገኙት፡፡ የተነጋገሩበት አጀንዳ በነጋታው “ኢፍቲን” ላይ ወጣ፡፡

ታስታውስ እንደሆነ “ህብረት” ሲመሠረት ስብሰባው ላይ ለመካፈል ዋሽንግተን ዲሲ ሄጄ ነበር፡፡ ውይይት ስናደርግ አንዳንድ የሀሣብ ግጭቶች ተፈጠሩ፡፡ በእኛና በኢህአፓዎች መካከል ልዩነቶች ሲፈጠሩ፣ ሀሣብን በሀሣብ ማሸነፍ ሲገባቸው አሉባልታ አስወሩብኝ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ አንድ የግል ጋዜጣ “አቶ ልደቱ የሕብረቱን ስብሰባ በቴፕ ሲቀዱ ተያዙ” ብሎ ዜና አወጣ፡፡ ስብሰባው አላለቀም፤ እዚያ ተቀምጠናል፡፡ በኋላ ተደውሎ ከኢትዮጵያ ተነገረኝ፡፡ በማግስቱ ስብሰባው ይቀጥል ስለነበር ወደ ስብሰባው ገብቼ “ኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ ተብሎ ተፅፏል፤ ይሄ ነገር ሀሰት መሆኑን አይታችኋል፤ ማስተካከል የለባችሁም ወይ?” ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ ኢህአፓዎች ይህንን ነገር ለመቀበልና ለማስተባበል አልፈለጉም፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ነገር ምላሽ አንሰጥም ተብሎ ታለፈ፡፡ ሀሳብን በሀሣብ ማሸነፍ ሲያቅታቸው እንዲህ ያስወሩብሃል፡፡

ሎሚ፡- ኢህአዴግ በወቅቱ አንተ በነበረህ ድጋፍ ተጠቅሞ በቅንጅት ውስጥ ልዩነት ፈጥረህ እንድትወጣ ግፊት አድርጓል ተብሏል፤ አንተ ስትወጣ ቅንጅት ለሁለት ይከፈላል ቢባልም ለግለሰብ ሳይሆን ለፓርቲ ቅድሚያ ተሰጥቷልም ተብሏል፤ ይህን ጉዳይስ እንዴት አየኸው;

ልደቱ፡– ሂደቱን የግል ጉዳይ አድርገህ አትየው፡፡ ልዩነቱ የተፈጠረው በእኔና በቅንጅት መካከል አይደለም፡፡ በኢዴፓና በቅንጅት ነው፡፡ እኔ ያራመድኳቸው ሀሳቦች የግል አቋሜ ሳይሆን በሙሉ ኢዴፓ ያመነባቸው ናቸው፡፡ ሌላ ውጫዊ አካል ተፅዕኖ አድርጐብን የያዝነው አይደለም፡፡ ያንጸባረቅነው መቶ በመቶ የምናምንበትን አቋም ነበር፡፡ ኢህአዴግ ስለገፋኝ ወይም ተፅዕኖ አድርጐብኝ አይደለም፡፡ አቋምህን ቀይር ተብዬ ተጠይቄም አላውቅም፡፡ ይሔ ልደቱን የኢህአዴግ ሰው ለማስመሰል የተደረገ ጉዳይ ነው፡፡

ከኢህአዴግ ጋር በፖለቲካ አቋም የምጣጣም ብሆን ኖሮ፣ ለእንደዚህ ዓይነቶቹ አሉባልተኞች በደንብ አድርጌ አሳያቸው ነበር፡፡ ኢህአዴግ መሆን ምንም ማለት እንዳልሆነ አሳያቸው ነበር፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ግን ኢህአዴግ መሆን አልችልም፡፡ የሚመኙትን ምኞት በደንብ በተግባር አሳያቸው ነበር፡፡ ኢህአዴግ የሆኑ ጓደኞች አሉኝ፡፡ እነሱ ያላቸውን አስተሳሰብ አከብራለሁ፡፡ ምርጫቸው ነው፡፡ ከእነሱ ውስጥ አንዱ ብሆን ምንድነው ችግሩ; ከስድስት ሚሊዮን የኢህአዴግ አባል አንዱ ብሆን ምን ችግር አለው; ያ የፖለቲካ አመለካከት ነው፡፡ ተቃዋሚም ሆኜ የተቃዋሚው ሚና ካልጣመኝ ሀሣቤን ከቀየርኩ ኢህአዴግ መሆን እኮ መብቴ ነው፡፡ ትናንት ተቃዋሚ ነበርክና ዛሬ የኢህአዴግ አባል መሆን የለብህም የሚባል ነገር የለም፡፡ ትናንት ኢህአዴግ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ተቃዋሚዎች ሆነው የለ እንዴ? እነ አቶ ስዬና ዶ/ር ነጋሶ እኮ ትናንት የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፡፡ በኋላ ተቃዋሚ ሆነዋል፡፡ ካመንኩበት እኔም ዛሬ ተቃዋሚ ሆኜ ነገ ኢህአዴግ ብሆን ምን ችግር አለው?…

…ይቀጥላል

Posted by Hellen Tesfaye

ግንቦት 7 ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ምላሽ ሰጠ – “ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል?”

አያ ጅቦ  ሳታመካኝ ብላኝ !!!

 

ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።

ኃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት ከቀረቡለት ብዙ ዲሪቶ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ አገር ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ነበር። ኃይለማሪያም አገር ቤት የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች “በራሳቸው የሚደረጉ ሳይሆኑ ከኋላ ባሉ ሌሎች ኃይሎች መሪነት የሚደረጉ” ናቸው ሲል ተናግሯል። ኃይለማሪያም ጌቶቹ ፊቱን በጨርቅ አስረዉት የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር፤ መከራና ስደት አልታይ ብሎት ነዉ አንጂ ወያኔን የመሰለ ነብሰ ገዳይ ባለበት አገር ዉስጥ የህዝብን ብሶት የሚያስጋቡ ጥያቄዎች በየቀኑ ይመነጫሉ አንጂ ከዉጭ አገርማ አይመጡም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄዉ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፈራቸዉ ዋሾ ሰዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴ የአሸባሪዎች እጅ ያለበትና፤አማኞቹ ሃይማኖታቸውን የወደዱ መስሏቸው ሳያውቁ የገቡበት ስለሆነ እንዲታረሙ እንመክራቸዋለንም” ብሏል። እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ፈጽሞ ሊረዳ አልቸለም፤ ስለዚህ ምክር የሚያስፈልገዉ መብትና ነጻነት ምን እንደሆኑ ገብቶት የሚታገለዉ የአትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኃይለማሪያም እራሱ ነዉ።

እኛ ግንቦት ሰባቶች ወያኔን የመሰለ ጨካኝ እና ምንም አይነት አገራዊ ኃላፊነት የማይሰማውን ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በሠላማዊ መንገድ የሚጋፈጡ ወገኖቻችንን እናደንቃለን። እነዚህ ወገኖቻችን ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደሚለው የማንንም አጀንዳ የተሸከሙ ሳይሆኑ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸውና ኃይለማሪያም በዉክልና ለሚያስረግጣቸዉ ወገኖቻችዉ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ጅግኖች ናቸዉ። አጀንዳቸውም የተደበቀ ወይም ከጀርባውም ሌላ ነገር ያለው አጀንዳ አይደለም።አጀንዳቸው ግልጽ እና የታወቀ የነፃነት፤ የእኩልነት፤የፍትህና የሠላም አጀንዳ ነው። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የዜጎችን ጥያቄ አድምጦ መልስ መስጠት ሲገባው እነዚህን የኢትዮጵያን ህዝብ አጀንዳ ተሸክመው የሚታገሉ ወገኖች ደካሞች አድርጎ ለመሳል የሚያደርገዉ ሙከራ አንድም በተቃዋሚዎቹ ዙሪያ የተሰባሰበውን የሰው ኃይል ካለማወቅ፤ አለዚያም ደግሞ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” እንደሚባለው ነገር ነው።

ሌላው ኃይለማሪያም የሚናገረዉ ቃል ጠፍቶት በተደጋጋሚ ሲንተባተብ የታየዉ በሽብርተኝነት አካባቢ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለስ ነዉ። በእኛ እይታ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋነኛው አገር በቀል አሸባሪ ህወሃት እና ህውሃት ብቻ ነው። ህወሃት ስልጣን ላይ ያቆየኛል ብሎ ከገመተ የማይመሰርተው የክስ ዓይነት፤ የማያፈሰው የንጹህ ሰው ደም ፤የማያፈነዳው የቦንብ እና የፈንጂ ዓይነት እንደሌለ ከሃውዜን እስከ አዲስ አበባ ያሉ መንገዶች ቋሚ ምስክሮች ናቸው። ይህንን እኩይ ተግባሩን ዓለም ሁሉ እንደሚያውቀው በዊክ-ሊክ ላይ የወጣው መረጃም አሳይቷል።

የህውሃት ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሠላማዊ ትግሉን ለማፈን ከፈለገ በትግሉ ዙሪያ የተሰባሰቡትን ዜጎች ከሌላ ከማንም ጋር ማነካካት አያስፈልገውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሁሉ አንደ ኃይለማሪያም ሞቶ የተቀበረን ሰዉ ራዕይ የተሸከሙ የአመለካከት ደሃዎች ሳይሆኑ የራሳቸው አስተሳሰብና ህያዉ ራዕይ ያላቸው ዜጎች ናቸው። አነዚህን ሠላማዊ ታጋዮች ከማይገናኝ ሌላ ኃይል ጋር አቆራኝቶ ለመምታት መሞከር ለኃይለማሪያምም ሆነ ለጌቶቹ አይበጃቸዉም። ዛሬ በወያኔ ነብሰ ገዳይ ወታደሮች ተከብቦ እዩኝ እዩኝ የሚለዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ የነደደ ቀን ደብቁኝ ማለት ይመጣልና ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት የበደለዉን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ የነጻነት ኃይሎችን እንዲቀላቀል ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን።

በመጨረሻም ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ስለ ግንቦት ሰባት ተጠይቆ ሲመልስ ግንቦት ሰባት “በህልም ውስጥ ያለ ድርጅት” ነው ብሏል። ታድያ ምነዉ ተኝቶ ህልም የሚያልም ድርጅት ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል? ለምንስ ይሆን ወያኔና ታማኝ ሎሌዉ ኃ/ማሪያም ያገኙትን ሁሉ ግንቦት ሰባት እያሉ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት? ያገኛችሁትን ሁሉ የግንቦት ሰባት አባል እያላችሁ ትከሳላችሁ? ለምንስ በግንቦት ሰባት ስም ታስራላችሁ? ትገርፋላችሁ? ትገድላላችሁ? ተኝቶ ለሚያንቀላፋ ድርጅት ለምን ትሸበራላችሁ፤ ለምንስ እንቅልፍ አጥታችሁ ትባዝናላችሁ? ግንቦት ሰባት እናንተ አልገባችሁም አንጂ መነሻውንና መድረሻውን አጥርቶ የሚያውቅ፤ ከደመናው ባሻገር ፍንትው ያለ የነፃነት ዉጋገን የሚታየው ባለ ታላቅ ራዕይ ድርጅት ነው። አስኪ ምናልባት ቢገባችሁ ተረት ቢጤ እንንገራችሁ፤

“አንዲት ሚዳቋ ነበርች አሉ። ሚዳቆ ከመሬት ገንዘብ ተበድራ ሲትኖር ከእለታት አንድ ቀን መሬት አፍ አውጥታ ብድሬን መልሽ አንጂ ብላ ትጠይቃታለች። ሚዳቆዋም ደንግጣ ከነበረችበት ቦታ ፈትለክ ብላ ወደ ተራራ ጫፍ ላይ ወጥታ እፎይ ያንን ድምጽ ከአሁን በኋላ አልሰማም አለች። መሬትም በይ ብሬን ክፈይኝ ስትል ዳግም ጠየቀቻት። እንዴ ይህች መሬት የሌለችበት ዬት አገር ሊሂድ ብላ ሚዳቆ ወደ ማይታወቅ ቦታ ተፈተለከች። ከዚያም እያለከለከች በቃ አሁንስ አታገኚኝም ስትል አሁንም መሬት ብቅ ብላ እየጠበኩሽ ነውኮ ብድሬን ክፈይ እንጂ ስትል ጠንከር አድርጋ ጠየቀቻት። ሚዳቆዋም መሬት የሌለችበት ልትደረስ ስትበር ስትበር ሳንባዋ ፈንድቶ ሞተች”ይባላል።

የፍትህ፤ የእኩልነት፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እንደ መሬት ናቸው። የትም ሂዱ፤ የትም ግቡ ይከተሏችኋል። መስጊድ ዉስጥ አሉ፤ ቤተክርስትያናት ውስጥ አሉ። ቤተመንግሰት ዉስጥም አሉ። የሌሉበት ቦታ የለም። መፍትሄው እንደ ሚዳቆዋ መሸሽ አይደለም። መፍትሄው ዜጎች የሚያነሷቸውን የፍትህ፤ የእኩልነ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን አድምጦ ትክክለኛ መልስ መስጠትና ከዕዳ ነጻ መሆን ብቻ ነዉ ። ከዚህ ዉጭ ጥያቄን ላለመስማት ወይም ሰምቶ ለመደፍጠጥ የሚደረገው ከንቱ ሩጫ መጨረሻው እንደ ሚዳቆዋ መፈንዳት እንጂ ህይወት አይሆንላችሁም።

እኛ ግንቦት ሰባቶች ዘረኛዉንና አሸባሪውንና የወያኔ ስርዐት ለመደምሰስና ህዝብ በነፃነት ያለፍርሃት የሚኖርበትን አገር ለመፍጠር ቆርጠን ተነስተናል። ከእንግዲህ የሚያቆመን ምንም ነገር የለም። የምንታገለዉ ለህዝብ ጥያቄያችንም ህዝባዊ ጥያቄ ነዉና እኛም አንደጥያቄዉ በየመስጊዱ፤ በየቤተክርሲቲያኑና በየሰፈሩ ዉስጥ አለን።እኛ የሌለንበት ስፍራ የለም። በዚህ አጋጣሚ የዘመናት ትግላችን ፍሬዉ የሚታይበት ቀን እጅግ በጣም ቅርብ ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አገር ተረካቢ የሆነዉ ወጣቱ ትዉልድ እራሱን፤ ወገኖቹንና እናት አገሩን ለማዳን የሚደረገዉን የነጻነት ትግል እየመጣ እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪያችንን አቅርበናል። ኑ እና ተቀላቀሉን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Posted by Hellen Tesfaye

አዲሱ የኢ/ት ፕ/ት ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ጀርባ ሲገለጥ

ከርዕሶም ኃይለ

ፕ/ት ሆነው የተመረጡት ሙላቱ ተሾመ ትምህርታቸውን በሰባዎቹ አመታት የተከታተሉትና “ዶ/ር” የሚል ማእረግ ያገኙት በቻይና ነው። በትምህርታቸው በጣም ደካማ ነበሩ። ሙላቱ ሁለት አመት ወድቀው ከመባረር የተረፉት በነዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አማካይነት ሲሆን፣ በወቅቱ ዶ/ር ነጋሶ ያሉበት ኮሚኒቲ ለዩኒቨርሲቲው ያቀረቡት የextension ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ መቀጠል እንደቻሉ፣ እንዲሁም ቻይና በነበሩ ጓደኞቻቸው እገዛ ለመጨረስና “ዶ/ር” ለመባል እንደበቁ፣ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምሁር በወቅቱ አጋልጠው ነበር። ምሁሩ ጉዳዩን ለማጋለጥ የተነሱት ዶ/ር ነጋሶ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቀረባቸውን ተከትሎ በስብሰባ ላይ « መንግስቱ ሃ/ማሪያምን መሰልከኝmulatu teshome» ሲሉ አቶ መለስ ዜናዊን ተናግረው ስብሰባውን ጥለው በመውጣታቸው፣ ከዚያም ዶ/ር ሙላቱ በያዙት አቋምና ጭራሽ «ነጋሶ መጠየቅና መታሰር አለበት» በማለት ከመለስ ወግነው በመናገራቸው ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል። ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ የረዷቸውና የኦ.ህ.ዴ.ድ አባል እንዲሆኑ ያደረጓቸው ዶ/ር ነጋሶ ሆነው ሳለ፣ ያን ሁሉ ውለታ ረስተውና በአደርባይነት ተሰልፈው እንዴት «ነጋሶ መታሰር አለበት» ብለው በጭፍን ይፈርዳሉ?..ሲሉ ምሁሩ በግርምት በወቅቱ ጠይቀዋል። ለአቶ መለስ ባሳዩት ታማኝነት ዶ/ር ነጋሶን ተክተው ፕ/ት እንዲሆኑ በወቅቱ ታጭተው የነበረ ቢሆንም፣ እንዲሰረዝ የተደረገው «የፓርቲ አባል ያልሆነ ነው ፕ/ት መሆን የሚችለው» የሚልና በተጨማሪ የቀድሞውን ፕ/ት ዶ/ር ነጋሶን ከፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ የሚያደርግ አሳፋሪ ህግ በመለስ እንዲወጣ በመደረጉ ነበር። ሌላው አነጋጋሪ ነጥብ ይህ አዋጅ ሳይሻር፣ ማለትም « የፓርቲ አባል ያልሆነ ግለሰብ ፕ/ት ይሆናል» የሚለው ህግ በአዋጅ ሳይሻር፥ የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑት ሙላቱ ተሾመ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው አስገራሚና ምን ያክል ለራሳቸው ህግና አዋጅ እንደማይገዙ የሚያሳይ ሆኗል። ዘ-ሐበሻ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ናት። በሌላም በኩል “ዶ/ር” ሙላቱ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት፣ መጋቢት 1996ዓ.ም ፓርቲው ባደረገው ግምገማ በአቶ መለስ ከተዘለፉት አንዱ ሲሆኑ፣ ጉዳዩን በመንተራስ «ኢትኦጵ» ጋዜጣ «ከሕወሐት መንደር ከቃረምኩት» በሚል አምዱ በወቅቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንደዘገበው፥ « አቶ መለስ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ “ ሙላቱ – አንተን ሚ/ር አድርጌ መሾሜን ረስቸዋለሁ። ያለስራ በሚ/ርነት የተጎለትክ ነህ፤ እዛው ጃፓን አምባሳደር እንደሆንክ ብትቀር ይሻላል። ..ኦ.ህ.ዴ.ድ ማለት ለትግል ፈጥረነው የት እንደገባ የማይታወቅ ድርጅት ነው።” » በማለት መለስ ዜናዊ መናገራቸውን አመልክቶ ነበር። የ“ዶ/ር” ሙላቱ ባለቤት ወ/ሮ መአዛ አብርሃም ትባላለች። ሸንቃጣዋና የደስ ደስ ያላት መአዛ አንድ ጃፓናዊ አግብታና ልጅ ወልዳ በቶኪዮ ከተማ ትኖር ነበር። እራሷን በጣም ስለምትጠብቅና አለባበሷን (አጭር ሚኒ ቁምጣ ነው የምትለብሰው) ለተመለከታት በወጣትነት የእድሜ ክልል እንደሆነች አድርጎ ይገምታታል፤ ሃቁ ግን ወ/ሮ መአዛ 53 አመት እድሜ ይሆናታል። ከሙላቱ ተሾመ ጋር የተዋወቁት ጃፓን ነበር። መአዛ በጣም ብልጥ ሴት ናት። በጃፓን የኢትዮጲያ አምባሳደር የነበሩት ሙላቱ ተሾመን ታጠምዳለች። ያጠመደችው ወላጅ አባቷ አቶ አብርሃም ነጋ በቀይ ሽብር ወንጀል ተከሰው ስለታሰሩ ነበር። ጃፓናዊ የልጇን አባት ባሏን በመግፋት አምባሰድሩን ትቀርባለች። እንዳጋጣሚ አቶ ተሾመ የስራ ጊዚያቸውን ጨርሰው አገር ቤት ሲመጡ አብራ ትመጣለች። ክዛም ወላጅ አባቷን እንዲያስፈታላት ትጠይቃለች። የተጠየቁት ሙላቱ « ይህን በጭራሽ አልችልም። እነመለስ ከሰሙ ከእንጀራዬ ወዲያው ያባርሩኛል። ይህን ጥያቄ ዳግም እንዳትጠይቂኝ።» ይላሉ። ወላጅ አባቷ በ2000ዓ.ም ከእስር ተፈቱ። ወ/ሮ መአዛ ጃፓናዊ ባሏንና ልጇን በመተው ለፈፀመችው የትዳር ማፍረስ ተግባር ወደዛች አገር ዳግም እንዳትገባ ውሳኔ ስለተላለፈባት፣ ከ”ዶ/ር” ሙላቱ ጋር መጠቃለልን መረጠች። መአዛና ሙላቱ አንድ ልጅ አፍርተዋል። ሙላቱ ተሾመ በ1994ዓ.ም በሰባት ሚሊዮን ብር በቦሌ ያስገነቡት ዘመናዊ ቪላ በወር 36ሺህ ብር እንደሚከራይ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ ቪላውን ለመገንባት ገንዘቡ በሙስና እንዲገኝ ትልቅ ሚና የተጫወቱት ባለቤታቸው ወ/ሮ መአዛ መሆናቸው ታውቋል።

Posted by Hellen Tesfaye